ከዚህም በኋላ ዐሥራ አራት ቀን በዓል አደረገላቸው።
ሚስቱ ዳቦ በብዛት እንድትጋግር ነገራት፤ ወደ ከብቶቹ መንጋ ሄደና ሁለት ሰንጋዎችና አራት ሙክቶች አምጥቶ ታርደው እንዲዘጋጁ አዘዘ፥ ዝግጅቱም ተጀመረ።