ራጉኤልም እግዚአብሔርን አመሰገነው፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ አንተ የተመሰገንህ ነህ፤ ንጽሕትና ቅድስት በሆነች ምስጋና ሁሉ የተመሰገንህ ነህ። ጻድቃንህ፦ በሠራኸው ሥራ ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ መላእክትህና የመረጥኻቸውም ሁሉ ለዘለዓለም ያመሰግኑሃል።
ከዚህ በኋላ ራጉኤል የሰማዩን አምለክ በእነዚህ ቃላት እንዲህ ሲል ባረከ “አምላኬ ሆይ ንጹሕ በሆነ በረከት አንተ ብሩክ ነህ፤ ለዘለዓለሙ ብሩክ ሁን።