ጠርቶም እንዲህ አለው፥ “ልጄ በሞትሁ ጊዜ በመልካሙ ቅበረኝ፤ እናትህንም ጠብቃት፤ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አክብራት፤ የወደደችውንም አድርግላት፤ አታሳዝናትም።
ስለዚህ ልጁን ጦቢያን ጠራና እንዲህ አለው፦ “ስሞት በክብር ቅበረኝ፥ እናትህን አክበራት፥ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ አትለያት፥ ደስ የሚላትን ሁሉ አድርግላት፥ በምንም ነገር አታሳዝናት፤