አባቱ ለሞተበት ልጅ እንደ አባት ሁነው፤ ለእናቱም እንደ ባሏ ቁምላት፤ እንደ ልዑልም ልጆች ትሆናለህ፥ ከእናትህም ይልቅ ይወድሃል።
አባት ለሌላቸው እንደ አባት፥ ለእናቶቻቸውም ደግሞ እንደ መልካም ባል ሁን። ታዲያ አንተም ለልዑል እግዚአብሔር እንደ ልጅ ትሆናለህ፤ ፍቅሩም ከእናትህ ፍቅር የበለጠ ነው።