ነገርን መስሎ በመናገር አይኖሩም፤ ነገር ግን ያገርን ፈቃድ ያጸናሉ፤ ጸሎታቸውም በሥራቸው ይራቀቁ ዘንድ ነው።
ባህላቸው ወይም ፍርዳቸው የሚመረጥ አይደለም፤ ከፈላስፎችም ዘንድ አዘውትረው አይቀርቡም፤ የምድርን ወጋግራዎች ይደግፋሉ፤ ጸሎታቸውም ስለ ሥራቸው ነው።