የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 90:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በላ​ባ​ዎቹ ይጋ​ር​ድ​ሃል፥ በክ​ን​ፎ​ቹም በታች ትተ​ማ​መ​ና​ለህ፤ እው​ነት እንደ ጋሻ ይከ​ብ​ብ​ሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሺሕ ዓመት በፊትህ፣ እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣ እንደ ሌሊትም እርቦ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓት ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለአንተ አንድ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ነው፤ አልፎ እንደ ሄደው እንደ ትናንት ነው፤ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓቶች ነው።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 90:4
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ አም​ላኬ፥ ብዙ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አደ​ረ​ግህ፥ አሳ​ብ​ህ​ንም ምንም የሚ​መ​ስ​ለው የለም፤ አወ​ራሁ፥ ተና​ገ​ርሁ፥ ከቍ​ጥ​ርም በዛ።


ንጋ​ትም በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳ​ትና በደ​መና ዐምድ ሆኖ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት አወከ።


ከሌሊቱም በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ።


“ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፤ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።


ከሌ​ሊቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወይም በሦ​ስ​ተ​ኛው ክፍል ቢመ​ጣና እን​ዲሁ ቢያ​ገ​ኛ​ቸው እነ​ዚያ አገ​ል​ጋ​ዮች ብፁ​ዓን ናቸው።


እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።


ጌዴ​ዎ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት መቶ ሰዎች በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው ትጋት መጀ​መ​ሪያ ዘብ ጠባ​ቂ​ዎች ሳይ​ነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ች​ንም ነፉ፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ማሰ​ሮ​ዎች ሰባ​በሩ፤