የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 40:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጠላ​ቶ​ቼም ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፥ በእኔ ላይም ክፋ​ትን ይመ​ክ​ራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ መጥቻለሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ተጽፏል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መሥዋዕትንና ቁርባንን አልወደድህም፥ የሚሰማ ጆሮ ሰጠኸኝ፥ የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልፈለግህም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ “ስለ እኔ በተጻፈው የሕግ መጽሐፍ መሠረት እነሆ እኔ መጥቻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 40:7
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአ​ን​ተና በሴ​ቲቱ መካ​ከል፥ በዘ​ር​ህና በዘ​ር​ዋም መካ​ከል ጠላ​ት​ነ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እርሱ ራስ​ህን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ አን​ተም ሰኰ​ና​ውን ትነ​ድ​ፋ​ለህ።”


ከኀ​ጢ​አቴ ፊት​ህን መልስ፥ በደ​ሌ​ንም ሁሉ ደም​ስ​ስ​ልኝ።


ጽድቅንና ቅን ፍርድን ማድረግ መሥዋዕት ከመሠዋት ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው።


የም​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በብ ምላ​ስን ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነ​ቃ​ኛል፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን ሰጥ​ቶ​ኛል።


የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣ​ጽም ጆሮ​ዬን ከፍ​ቶ​አል፤ እኔም ዐመ​ፀኛ አል​ነ​በ​ር​ሁም፤ አል​ተ​ከ​ራ​ከ​ር​ሁም።


እር​ሱም ከሙ​ሴና ከነ​ቢ​ያት፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍ​ትም ሁሉ ስለ እርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ጀመር።


እር​ሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነ​ቢ​ያ​ትና በመ​ዝ​ሙ​ርም ስለ እኔ የተ​ነ​ገ​ረው ይፈ​ጸም ዘንድ እን​ዳ​ለው፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ የነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላ​ቸው።


መጻ​ሕ​ፍ​ትን መር​ምሩ፤ በእ​ነ​ርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የም​ታ​ገኙ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እነ​ር​ሱም የእኔ ምስ​ክ​ሮች ናቸው።


ለሚ​ያ​ም​ኑ​በ​ትም ሁሉ ኀጢ​አ​ታ​ቸው በስሙ እን​ደ​ሚ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ነቢ​ያት ሁሉ ምስ​ክ​ሮቹ ናቸው።”


ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።