የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 14:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በአ​ን​ደ​በቱ የማ​ይ​ሸ​ነ​ግል፥ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ክፋ​ትን የማ​ያ​ደ​ርግ፥ ዘመ​ዶ​ቹ​ንም የማ​ያ​ሰ​ድብ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤ በአንድነትም ተበላሹ፤ መልካም የሚያደርግ የለም፤ አንድ እንኳ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁሉም ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ፥ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፥ አንድም እንኳ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ሁሉም ባዝነዋል፤ ሁሉም በአንድነት ተበላሽተዋል፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ መልካም ነገርን የሚያደርግ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 14:3
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን እንደ ተበ​ላ​ሸች፥ ሥጋን የለ​በሱ ሁሉም በም​ድር ላይ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን እንደ አበ​ላሹ አየ።


ከር​ኵ​ሰት የሚ​ነጻ ማን ነው? አንድ ስንኳ የለም።


ይል​ቁ​ንስ አስ​ጸ​ያ​ፊና የረ​ከሰ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እንደ ውኃ የሚ​ጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?


አቤቱ፥ በድ​ን​ኳ​ንህ ውስጥ ማን ያድ​ራል? በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ተራ​ራህ ማን ይኖ​ራል?


የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።


እነሆ፥ ዘመ​ኖቼን አስ​ረ​ጀ​ሃ​ቸው፤ አካ​ሌም በፊ​ትህ እንደ ኢም​ንት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።


እነሆ፥ ነፍ​ሴን አድ​ድ​ነ​ዋ​ታ​ልና፥ ብር​ቱ​ዎ​ችም በላዬ ተነሡ፤ አቤቱ፥ በበ​ደ​ሌም አይ​ደ​ለም፥ በኀ​ጢ​አ​ቴም አይ​ደ​ለም።


ፈር​ዖ​ንም፥ ሹሞ​ቹም ሁሉ፥ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ሁሉ በሌ​ሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌ​ለ​በት ቤት አል​ነ​በ​ረ​ምና በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ታላቅ ልቅሶ ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ እንደ አለ አደ​ረገ፤ የው​ሻ​ው​ንም ዝንብ ከፈ​ር​ዖን፥ ከሹ​ሞ​ቹም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አራቀ፤ አንድ ስንኳ አል​ቀ​ረም።


በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጊ​ዜው ሰዎ​ችን ቅኖች አድ​ርጎ እንደ ሠራ​ቸው እነሆ፥ ይህን ብቻ አገ​ኘሁ፥ እነ​ርሱ ግን ብዙ ዕው​ቀ​ትን ይሻሉ።


እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።


ሁላ​ችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነ​ናል፤ ጽድ​ቃ​ች​ንም ሁሉ እንደ መር​ገም ጨርቅ ነው፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ምክ​ን​ያት እንደ ቅጠል ረግ​ፈ​ናል፤ እን​ዲ​ሁም ነፋስ ጠራ​ርጎ ወስ​ዶ​ናል።


ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገ​ሮ​ችን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የሕ​ይ​ወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተ​ው​ኛል፥ የተ​ነ​ደ​ሉ​ትን ውኃ​ው​ንም ይይዙ ዘንድ የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ጕድ​ጓ​ዶች ለራ​ሳ​ቸው ቈፍ​ረ​ዋል።


ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ።


በዚ​ህም ልዩ​ነት የለም፤ ሁሉም ፈጽ​መው በድ​ለ​ዋ​ልና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማክ​በ​ር​ንም ትተ​ዋ​ልና።


ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ ስዘ​ል​ፋ​ችሁ ነው፤ እን​ግ​ዲህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸሁ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾ​ችን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ማስ​ታ​ረቅ የሚ​ችል ሽማ​ግሌ የለ​ምን?


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለ​ሆን ራሳ​ች​ንን እና​ንጻ፤ ሥጋ​ች​ንን አና​ር​ክስ፤ ነፍ​ሳ​ች​ን​ንም አና​ሳ​ድፍ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት የም​ን​ቀ​ደ​ስ​በ​ትን እን​ሥራ።


እኛ ሁላ​ችን ቀድሞ እንደ ሥጋ​ችን ምኞት ኖርን፤ የሥ​ጋ​ች​ን​ንም ፈቃ​ድና ያሰ​ብ​ነ​ውን አደ​ረ​ግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥ​አ​ንም ሁሉ የጥ​ፋት ልጆች ሆንን።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ እሰ​ጣት ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር ከእ​ነ​ዚህ ሰዎች ማንም አያ​ይም፥