የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ሰውም በአ​ጠ​ገቡ ድን​ገት ቢሞት የራሱ ብፅ​ዐት ይረ​ክ​ሳል፤ እርሱ በሚ​ነ​ጻ​በት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ይላ​ጨው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ድንገት ሰው አጠገቡ ሞቶ ለእግዚአብሔር የተለየበትን ጠጕሩን ቢያረክስበት፣ በሚነጻበት ዕለት ማለት በሰባተኛው ቀን ጠጕሩን ይላጭ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት እርሱም የተቀደሰውን ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጫል፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“በድንገት አንድ ሰው በአጠገቡ ቢሞት፥ የተቀደሰውን ራሱንም ቢያረክስ፥ በሰባተኛው ቀን ራሱን ይላጭ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የተለየውንም ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 6:9
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ ያገ​ለ​ግል ዘንድ ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ወደ መቅ​ደሱ በሚ​ገ​ባ​በት ቀን የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የነ​ጻ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ጠጕ​ሩ​ንም ሁሉ ይላ​ጫል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀ​መ​ጣል።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ጠጕ​ሩን ሁሉ ይላ​ጫል፤ ራሱ​ንም፥ ጢሙ​ንም፥ ቅን​ድ​ቡ​ንም፥ የገ​ላ​ው​ንም ጠጕር ሁሉ ይላ​ጫል፤ ልብ​ሱ​ንም፥ ገላ​ው​ንም በውኃ ያጥ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።


የተ​ሳ​ለ​ውም የተ​ሳ​ለ​ውን የራስ ጠጕር በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አጠ​ገብ ይላ​ጫል፤ የስ​እ​ለ​ቱ​ንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በታች ወዳ​ለው እሳት ይጥ​ለ​ዋል።


በብ​ፅ​ዐቱ ወራት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ነውና።


ጳው​ሎ​ስም እንደ ገና በወ​ን​ድ​ሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሰ​ላ​ምም ሸኙ​ትና ወደ ሶርያ በባ​ሕር ተጓዘ፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም አብ​ረ​ውት ነበሩ፤ ስእ​ለ​ትም ነበ​ረ​በ​ትና በክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ራሱን ተላጨ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከእ​ስያ የመጡ አይ​ሁድ ጳው​ሎ​ስን በመ​ቅ​ደስ አዩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ በእ​ርሱ ላይ አነ​ሳ​ሥ​ተው ያዙት።


ወደ ቤትህ ታመ​ጣ​ታ​ለህ፤ ራስ​ዋ​ንም ትላ​ጫ​ታ​ለህ፤ ጥፍ​ር​ዋ​ንም ትቈ​ር​ጥ​ላ​ታ​ለህ፤