Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 6:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የተ​ሳ​ለ​ውም የተ​ሳ​ለ​ውን የራስ ጠጕር በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አጠ​ገብ ይላ​ጫል፤ የስ​እ​ለ​ቱ​ንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በታች ወዳ​ለው እሳት ይጥ​ለ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ ‘ከዚያም ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጨው፤ ጠጕሩንም ወስዶ ከኅብረቱ መሥዋዕት ሥር በሚነድደው እሳት ውስጥ ይጨምረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ናዝራዊውም የተቀደሰውን የራሱን ጠጉር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጫል፥ የተቀደሰውንም ራስ ጠጉር ወስዶ ከአንድነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በመገናኛው ድንኳን በር መግቢያ ላይ ናዝራዊው ጠጒሩን ላጭቶ የአንድነት መሥዋዕት በሚቃጠልበት እሳት ላይ ያኖረዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ናዝራዊውም የተለየውን የራሱን ጠጕር በመገናኛው ድንኳን አጠገብ ይላጫል፥ የመለየቱንም ራስ ጠጕር ወስዶ ከደኅንነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 6:18
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አው​ራ​ው​ንም በግ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከሌ​ማቱ ቂጣ እን​ጀራ ጋር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም ደግሞ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና የመ​ጠ​ጡን ቍር​ባን ያቀ​ር​ባል።


“ራሱን ለመ​ለ​የት ስእ​ለት ባደ​ረ​ገ​በት ወራት ሁሉ ራሱን አይ​ላጭ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለ​የ​በት ወራት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ቅዱስ ይሆ​ናል፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ያሳ​ድ​ጋል።


“ሰውም በአ​ጠ​ገቡ ድን​ገት ቢሞት የራሱ ብፅ​ዐት ይረ​ክ​ሳል፤ እርሱ በሚ​ነ​ጻ​በት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ይላ​ጨው።


እን​ዲሁ እና​ን​ተም ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ር​ጋ​ችሁ ‘እኛ ሥራ ፈቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ነን፤ ለመ​ሥ​ራ​ትም የሚ​ገ​ባ​ንን ሠራን’ በሉ።”


ጳው​ሎ​ስም እንደ ገና በወ​ን​ድ​ሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሰ​ላ​ምም ሸኙ​ትና ወደ ሶርያ በባ​ሕር ተጓዘ፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም አብ​ረ​ውት ነበሩ፤ ስእ​ለ​ትም ነበ​ረ​በ​ትና በክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ራሱን ተላጨ።


ስለ​ዚ​ህም ይህን የም​ል​ህን አድ​ርግ፦ ብፅ​ዐት ያላ​ቸው አራት ሰዎች በእኛ ዘንድ አሉ።


ይዘ​ሃ​ቸው ሂድ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ራስ​ህን አንጻ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ላጩ ስለ እነ​ርሱ ገን​ዘብ ክፈ​ል​ላ​ቸው፤ የሚ​ያ​ሙ​ህም በሐ​ሰት እንደ ሆነ፥ አን​ተም የኦ​ሪ​ትን ሕግ እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ ሁሉም ያው​ቃሉ።


ያን​ጊ​ዜም ጳው​ሎስ ሰዎ​ችን ይዞ በማ​ግ​ሥቱ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነጻ። የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ው​ንም ወራት መድ​ረ​ሱን ከነ​ገ​ራ​ቸው በኋላ ሁሉም እየ​አ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ይዞ​አ​ቸው ገባ።


በሚ​ወ​ደው ልጁ የሰ​ጠን የጸ​ጋው ክብር ይመ​ሰ​ገን ዘንድ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች