በአዕማዱም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዋንዛ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፤ አዕማዱም በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት፥ በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት የሆኑ አርባ አምስት ነበሩ።
ዘኍል 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከወንድ እስከ ሴት ከሰፈሩ አውጡአቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድም ሆነ ሴት አስወጡ፤ እኔ በመካከላቸው የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈር አስወጧቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንዱንና ሴቱን አውጡ፤ እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈሩ አወጡአቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመካከላቸው እኔ የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ፥ እነዚህን ያልነጹ ሰዎች ሁሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ከመካከላችሁ ወጥተው እንዲባረሩ አድርጉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንዱንና ሴቱን አውጡ፤ እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈሩ አወጡአቸው። |
በአዕማዱም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዋንዛ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፤ አዕማዱም በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት፥ በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት የሆኑ አርባ አምስት ነበሩ።
የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ጠጕሩንም ሁሉ ይላጫል፤ በውኃም ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል። ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።
“እንዲሁም በእነርሱ መካከል ያለችውን ድንኳኔን ባረከሱ ጊዜ፥ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው አንጹአቸው።
በሙሴና በአሮን ላይ ተነሡ፤ “ለእናንተ ይበቃችኋል፤ ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና፤ በእግዚአብሔርስ ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?” አሉአቸው።
እናንተ በውስጥዋ የምትኖሩባትን፥ እኔም ከእናንተ ጋር የማድርባትን ምድር አታርክሱኣት፤ በእስራኤል ልጆች መካከል የማድር እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ከሰፈሩ አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ።
አምላክህ እግዚአብሔር ሊያድንህ፥ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈርህ ውስጥ ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን።
ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኀጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።
ታላቅም ድምፅ ከሰማይ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤