ዘኍል 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነርሱም ላይ ቀይ መጐናጸፊያ ይዘርጉ፤ በአቆስጣውም ቍርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት። መሎጊያዎቹንም ያግቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚህም ላይ ቀይ ጨርቅ ይዘርጉ፤ የአቆስጣውን ቍርበት ደርበውም መሎጊያዎቹን በየቦታቸው ያስገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነርሱም ላይ ቀይ መጐናጸፊያ ይዘርጉ፥ በአስቆጣውም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሁሉ በቀይ ጨርቅ ሸፍነው ከበላዩ የተለፋ ስስ ቊርበት ይደርቡ፤ መሎጊያዎችንም ያስገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነርሱም ላይ ቀይ መጐናጸፊያ ይዘርጉ፥ በአቆስጣውም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ። |
ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፤ የሚያበሩባትንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎችዋንም፥ መኰስተሪያዎችዋንም፥ የኵስታሪ ማድረጊያዎችዋንም፥ እርስዋንም ለማገልገል የዘይቱን ማሰሮዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤