የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ አሮ​ንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህ​ናቱ ታገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተለ​ይ​ተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሌዋውያኑን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፤ እነርሱም ከእስራኤላውያን ተለይተው ለርሱ ፈጽመው የተሰጡ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሌዋውያንንም ለአሮንና ለልጆቹ ትሰጣለህ፤ ከእስራኤል ልጆች መካከል ለእርሱ ፈጽሞ የተሰጡ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእስራኤላውያን ሁሉ ተለይተው ለአሮንና ለልጆቹ ያገለግሉ ዘንድ ሌዋውያንን መድባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሌዋውያንንም ለአሮንና ለልጆቹ ትሰጣለህ፤ ከእስራኤል ልጆች ለእርሱ ፈጽመው ተሰጡ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 3:9
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያን ጊዜም ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከሙ ዘንድ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ረ​ጣ​ቸው ከሌ​ዋ​ው​ያን በቀር ማንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም” አለ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹና ልጆቹ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ከቀ​ዓት ልጆች ዘማ​ሪው ኤማን ነበረ፤ እር​ሱም የኢ​ዩ​ኤል ልጅ፥ የሳ​ሙ​ኤል ልጅ፤


ናታ​ኒም፤ የሲሓ ልጆች፥ የሐ​ሡፊ ልጆች፥ የጠ​ብ​ዖት ልጆች፤


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።


ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ዳዊ​ትና አለ​ቆቹ ከሰ​ጡ​አ​ቸው ናታ​ኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሃያ ናታ​ኒ​ምን አመጡ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ በስም በስ​ማ​ቸው ተሰ​በ​ሰቡ።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ለይቶ የመ​ረ​ጣ​ች​ሁን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እን​ድ​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉ​አ​ቸ​ውም በማ​ኅ​በሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁን ታሳ​ን​ሱ​ታ​ላ​ች​ሁን?


ደግ​ሞም የአ​ባ​ት​ህን የሌ​ዊን ነገድ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ወደ አንተ ሰብ​ስብ፤ ከአ​ን​ተም ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ያገ​ል​ግ​ሉ​ህም፤ አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ትሆ​ና​ላ​ችሁ።


እንደ ድን​ኳኑ ሥራ​ዎች ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ዕቃና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ ይጠ​ብቁ።


እን​ዲሁ ሌዋ​ው​ያ​ንን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ፤ እነ​ር​ሱም ለእኔ ይሁኑ።


እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ራት ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ በሚ​ወ​ለድ ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስ​ጄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወስ​ጄ​አ​ለሁ።


ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ስጦታ አድ​ርጌ አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ልዩ በሆ​ነች ድን​ኳን ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ኀጢ​አት ያቃ​ልሉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ተሰጡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ መቅ​ደስ የሚ​ቀ​ርብ አይ​ኑር።”


እር​ሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦ​ቹም ሐዋ​ር​ያ​ትን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነቢ​ያ​ት​ንና የወ​ን​ጌል ሰባ​ኪ​ዎ​ችን፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንና መም​ህ​ራ​ንን ሾመ።


“ምር​ኮን ማር​ከህ ወደ ሰማይ ወጣህ፤ ጸጋ​ህ​ንም ለሰው ልጅ ሰጠህ” ይላ​ልና።