የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 22:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሞ​ዓብ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የም​ድ​ያም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም የም​ዋ​ር​ቱን ዋጋ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለ​ዓ​ምም መጡ፤ የባ​ላ​ቅ​ንም ቃል ነገ​ሩት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሞዓብና የምድያም ሽማግሌዎችም ለሟርት የሚከፈለውን ዋጋ ይዘው ሄዱ፤ በለዓም ዘንድ በደረሱ ጊዜም የባላቅን መልእክት ነገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም ለምዋርቱ የሚከፈለውን ገንዘብ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃላት ነገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ የሞአባውያንና የምድያማውያን ሽማግሌዎች ስለ ርግማን የሚከፈለውን ገንዘብ ይዘው ወደ በለዓም በመሄድ የባላቅን መልእክት ሰጡት፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃል ነገሩት።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 22:7
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አለ​ቆ​ችሽ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና የሌ​ቦች ባል​ን​ጀ​ሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወ​ድ​ዳሉ፤ ፍር​ድ​ንም ሊያ​ጣ​ምሙ ይፈ​ል​ጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይ​ፈ​ር​ዱም፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም አቤ​ቱታ አያ​ዳ​ም​ጡም።


ሁሉም ከቶ የማ​ይ​ጠ​ግቡ የረ​ከሱ ውሾች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ያስ​ተ​ውሉ ዘንድ የማ​ይ​ችሉ ክፉ​ዎች ናቸው፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለ​ዋል።


ከንቱ ነገ​ርን ለሚ​ሰ​ሙት ሕዝቤ እየ​ዋ​ሻ​ችሁ ሞት የማ​ይ​ገ​ባ​ቸ​ውን ነፍ​ሳት ትገ​ድሉ ዘንድ፥ በሕ​ይ​ወ​ትም መኖር የማ​ይ​ገ​ባ​ቸ​ውን በሕ​ይ​ወት ታኖሩ ዘንድ ስለ ጭብጥ ገብ​ስና ስለ ቍራሽ እን​ጀራ ሕዝ​ቤን አር​ክ​ሳ​ች​ኋል።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ምዋ​ር​ቱን ያም​ዋ​ርት ዘንድ፥ በት​ሩን ያነሣ ዘንድ፥ ጣዖ​ቱ​ንም ይጠ​ይቅ ዘንድ በሁ​ለት መን​ገ​ዶች ራስ ላይ ይቆ​ማል።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።


እር​ሱም፥ “ዛሬ ሌሊት በዚህ እደሩ፤ እግ​ዚ​እ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው፤ የሞ​ዓብ አለ​ቆ​ችም በበ​ለ​ዓም ዘንድ አደሩ።


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ጥን​ቆላ የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ምዋ​ርት የለም፤ በየ​ጊ​ዜው ስለ ያዕ​ቆ​ብና ስለ እስ​ራ​ኤል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አደ​ረገ? ይባ​ላል።


በለ​ዓ​ምም እስ​ራ​ኤ​ልን መባ​ረክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካም እንደ ሆነ ባየ ጊዜ፥ እንደ ልማዱ ለማ​ሟ​ረት ወደ ፊት አል​ሄ​ደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን መለሰ።


እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤


እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።


ሟር​ተ​ኛ​ውን የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ም​ንም በአ​ን​ድ​ነት በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።


ቅንን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ የባሶርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ እርሱ የዐመፃን ደመወዝ ወደደ፤


ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፤ ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፤ በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።