የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለማ​ኅ​በ​ሩም ውኃ አል​ነ​በ​ረም፤ ሕዝ​ቡም በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ለማኅበረ ሰቡ የሚሆን ውሃ አልነበረም፤ ሕዝቡም ሙሴንና አሮንን በመቃወም ተሰበሰቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም፤ እነርሱም በሙሴና በአሮን ላይ ተሰበሰቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሰፈሩበት ቦታ ውሃ አልነበረም፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሙሴንና አሮንን በመቃወም ተሰብስበው፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም፤ በሙሴና በአሮንም ላይ ተሰበሰቡ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 20:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአ​ሕ​ዛብ ጉባኤ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጉ​ታል፥ በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሸንጎ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማን​ጐ​ራ​ጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ማለ​ዳም እን​ጀ​ራን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ጥዋት ታያ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​ትን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ በእ​ኛም ላይ የም​ታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ እኛ ምን​ድን ነን?” አሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከም​ን​ሞት በግ​ብፅ ምድር ሳለን ብን​ሞት በተ​ሻ​ለን ነበር።


ነገር ግን እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አታ​ምፁ፤ እኛ እና​ጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ንና የም​ድ​ሪ​ቱን ሰዎች አት​ፍሩ፤ ጊዜ​አ​ቸው አል​ፎ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኛ ጋር ነው፤ አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው።


ቆሬም ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ደጃፍ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ተገ​ለጠ።


በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተነሡ፤ “ለእ​ና​ንተ ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ማኅ​በሩ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነውና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ጉባኤ ላይ ለምን ትታ​በ​ያ​ላ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ማኅ​በሩ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ከበ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ ደመ​ናው ሸፈ​ናት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለጠ።


ሕዝ​ቡም፥ “በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ኸን?” ብለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሙሴ​ንም አሙ። “እን​ጀራ የለም፤ ውኃም የለ​ምና፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ንም ይህን ጥቅም የሌ​ለው እን​ጀራ ተጸ​የ​ፈች” ብለው ተና​ገሩ።