Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 21:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሕዝ​ቡም፥ “በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ ከግ​ብፅ ለምን አወ​ጣ​ኸን?” ብለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሙሴ​ንም አሙ። “እን​ጀራ የለም፤ ውኃም የለ​ምና፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ንም ይህን ጥቅም የሌ​ለው እን​ጀራ ተጸ​የ​ፈች” ብለው ተና​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ተነሥተው፣ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብጽ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ! ውሃ የለ! ይህን የማይረባ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል” ሲሉ ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሕዝቡም በጌታና በሙሴ ላይ እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃም የለም፤ ሰውነታችንም ይህን የሚያንገሸግሽ እንጀራ ተጸየፈ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ክፉ ቃል በመናገር እንዲህ ሲሉ አጒረመረሙ፤ “ምግብና ውሃ በሌለበት በዚህ በረሓ እንሞት ዘንድ ከግብጽ ምድር ለምን አወጣችሁን? ይህን አስከፊ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል!”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሕዝቡም በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ፦ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃ የለም፤ ሰውነታችንም ይህን ቀላል እንጀራ ተጸየፈ ብለው ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 21:5
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ፥ የሚ​ሹህ በእኔ አይ​ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉህ በእኔ አይ​ነ​ወሩ።


ሙሴ​ንም አሉት፥ “በግ​ብፅ መቃ​ብር ስላ​ል​ኖረ በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ አወ​ጣ​ኸን? ከግ​ብፅ ታወ​ጣን ዘንድ ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው?


ሕዝ​ቡም፥ “ምን እን​ጠ​ጣ​ለን?” ብለው በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ዩት ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ምን​ድን ነው?” ተባ​ባሉ። ያ ምን እን​ደ​ሆነ አላ​ወ​ቁ​ምና። ሙሴም አላ​ቸው፥ “ትበሉ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጣ​ችሁ እን​ጀራ ይህ ነው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስሙን መና ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነጭ ነው፤ ጣዕ​ሙም እንደ ማር እን​ጀራ ነው።


ልጆ​ቻ​ቸው ግን አማ​ረ​ሩኝ፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ፍር​ዴን ጠብ​ቀው አላ​ደ​ረ​ጉ​ትም፤ በሥ​ር​ዐ​ቴም አል​ሄ​ዱም፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አረ​ከሱ፤ በዚ​ህም ጊዜ፦ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም በም​ድረ በዳ እፈ​ጽ​ም​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


ነገር ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ያለ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ች​ኋ​ልና፥ በፊ​ቱም፦ ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን? ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሳ​ች​ኋ​ልና በአ​ፍ​ን​ጫ​ችሁ እስ​ኪ​ወጣ መር​ዝም እስ​ኪ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።”


በነ​ጋ​ውም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕዝብ ገድ​ላ​ች​ኋል” ብለው በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሙሴን አሉት፥ “እነሆ፥ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ጠ​ፋ​ለን፤ ሁላ​ች​ንም እና​ል​ቃ​ለን።


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ ተፈ​ታ​ተ​ኑት፥ ነዘር እባ​ብም እንደ አጠ​ፋ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አን​ፈ​ታ​ተን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች