Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ማኅ​በሩ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ከበ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ ደመ​ናው ሸፈ​ናት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ማኅበሩም ሙሴንና አሮንን ለመቃወም በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን ዘወር ሲሉ ደመና ድንኳኑን በድንገት ሸፍኖት አዩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 እንዲህም ሆነ፤ ማኅበሩ በሙሴና በአሮን ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን ዘወር ብለው ተመለከቱ፤ እነሆም፥ ደመናው ሸፈነው፥ የጌታም ክብር ተገለጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ሙሴንና አሮንን ለመቃወም ሁሉም በአንድነት ከተሰበሰቡ በኋላ ወደ መገናኛው ድንኳን ዞር ብለው ሲመለከቱ ደመናው የመገናኛውን ድንኳን ሸፍኖት የእግዚአብሔር ክብር ተገለጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 እንዲህም ሆነ፤ ማኅበሩ በሙሴና በአሮን ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን አዩ፤ እነሆም፥ ደመናው ሸፈነው፥ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:42
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቆሬም ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ደጃፍ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ተገ​ለጠ።


ሙሴና አሮ​ንም ከማ​ኅ​በሩ ፊት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ሄደው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወደቁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው።


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ገቡ፤ ወጡም፤ ሕዝ​ቡ​ንም ባረኩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለሕ​ዝቡ ሁሉ ተገ​ለጠ።


ማኅ​በሩ ሁሉ ግን “በድ​ን​ጋይ እን​ው​ገ​ራ​ቸው” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ተገ​ለጠ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመ​ና​ውም ስድ​ስት ቀን ሸፈ​ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​መ​ናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።


አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታ​ቸ​ውን አቀኑ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በደ​መ​ናው ታየ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ጥዋት ታያ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​ትን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ በእ​ኛም ላይ የም​ታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ እኛ ምን​ድን ነን?” አሉ።


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ገቡ።


ለማ​ኅ​በ​ሩም ውኃ አል​ነ​በ​ረም፤ ሕዝ​ቡም በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች