የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሙ​ሴም ላይ ተነሡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በም​ክር የተ​መ​ረጡ፥ ዝና​ቸ​ውም የተ​ሰማ ሁለት መቶ አምሳ የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴን ተቃወሙት። ከእነዚህም ጋራ ታዋቂ የማኅበረ ሰቡ መሪዎች የሆኑና በጉባኤ አባልነት የተመረጡ ሁለት መቶ ዐምሳ እስራኤላውያን ዐብረው ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች የሆኑ ከጉባኤው የተመረጡ፥ በዝናቸውም የገነኑ የማኅበሩ አለቆች ጋር በመሆን እነርሱ በሙሴ ላይ ተነሡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእነርሱም ጋር በእስራኤላውያን ዘንድ ዝናቸው የታወቀና ለሕዝብ መሪነት የተመረጡ ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎችን ወስደው በሙሴ ላይ ተነሡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ወሰዱ፤ ከጉባኤው የተመረጡ ዝናቸውም የተሰማ የማኅበሩ አለቆች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 16:2
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ።


ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን የሆኑ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት የታ​ወቁ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሃያ ሺህ ስም​ንት መቶ ነበሩ።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይስዔ፥ ኤሊ​ኤል፥ ዓዝ​ር​ኤል፥ ኢይ​ር​ምያ፥ ሆዳ​ይዋ፥ ኢየ​ድ​ኤል፤ እነ​ርሱ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን የታ​ወቁ ሰዎች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ።


ባንቺ ላይ ከአ​ኖ​ር​ኋት ከክ​ብሬ የተ​ነሣ ውበ​ትሽ ፍጹም ነበ​ረና ስምሽ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተሰማ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ገለጡ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ዋ​ንም ማር​ከው ወሰዱ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋና በሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ላይ በቀ​ልን ስላ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ቸው በሴ​ቶች መካ​ከል መተ​ረቻ ሆነች።


ከማ​ኅ​በሩ የተ​መ​ረጡ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ አለ​ቆ​ችና መሳ​ፍ​ንት በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።”


ሙሴም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ቱን ሴት አግ​ብ​ቶ​አ​ልና ባገ​ባት በኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ዊቱ ሴት ምክ​ን​ያት ማር​ያ​ምና አሮን አሙት።


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።


የኤ​ል​ያ​ብም ልጆች፥ ናሙ​ኤል፥ ዳታን፥ አቤ​ሮን፤ እነ​ዚ​ህም ከማ​ኅ​በሩ የተ​መ​ረጡ ነበሩ፤ ከቆሬ ወገን ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተጣሉ፤


“አባ​ታ​ችን በም​ድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢ​አት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገን መካ​ከል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ዶ​ችም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም።