Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የእግዚአብሔርም ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ተገናኝተው ልጆች በወለዱ ጊዜም ሆነ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንቱ ዘመን በጀግንነታቸው ከፍ ያለ ዝና ያተረፉ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በዚያን ዘመን ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፥ እና ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፥ እነርሱም በዱሮ ዘመን፥ ስማቸው የታወቀ፥ ኃያላን ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በዚያን ዘመንና ከዚያም በኋላ ከሰዎች ሴቶች ልጆችና ከእግዚአብሔር ልጆች ተዳቅለው የተወለዱ “ኔፊሊም” የሚባሉ ግዙፎች ሰዎች ነበሩ። እነርሱ በጥንት ዘመን በጀግንነታቸው የታወቁ ዝነኞች ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኂያላን ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 6:4
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ለእኛ ከተ​ማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ግንብ እን​ሥራ፤ በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ሳን​በ​ተን ስማ​ች​ንን እና​ስ​ጠ​ራው” ተባ​ባሉ።


በዚ​ያም ግዙ​ፋን የሆ​ኑ​ትን አየን፤ እኛም በእ​ነ​ርሱ ፊት እንደ አን​በ​ጣ​ዎች ሆን፤ እን​ዲ​ሁም በፊ​ታ​ቸው ነበ​ርን፤” እያሉ የሰ​ለ​ሉ​አ​ትን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አስ​ፈሪ አደ​ረ​ጓት።


በሙ​ሴም ላይ ተነሡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በም​ክር የተ​መ​ረጡ፥ ዝና​ቸ​ውም የተ​ሰማ ሁለት መቶ አምሳ የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።


እነ​ር​ሱም ደግሞ እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ራፋ​ይም ተብ​ለው ይታ​ወቁ ነበር፤ ሞዓ​ባ​ው​ያን ግን “ኦሚን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸው ነበር።


ከራ​ፋ​ይ​ንም ወገን የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አል​ጋው የብ​ረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአ​ሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝ​መቱ ዘጠኝ ክንድ ወር​ዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሰፈር የጌት ሰው ጎል​ያድ፥ ቁመ​ቱም ስድ​ስት ክንድ ከስ​ን​ዝር የሆነ፥ ኀይ​ለኛ ሰው መጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች