የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሌ​ዊም ልጅ የቀ​ዓት ልጅ የይ​ስ​ዓር ልጅ ቆሬ ከኤ​ል​ያብ ልጆች ከዳ​ታ​ንና ከአ​ቤ​ሮን፥ ከሮ​ቤ​ልም ልጅ ከፋ​ሌት ልጅ ከአ​ው​ናን ጋር ተና​ገረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሌዊ ልጅ፣ የቀዓት ልጅ፣ የይስዓር ልጅ የሆነው ቆሬ፣ ከሮቤልም ነገድ የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን እንዲሁም የፍሌት ልጅ ኦን በክፋት ተነሣሥተው፣

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ የኤልያብ ልጆች ዳታንንና አቤሮንን ከሮቤልም ልጆች የፋሌት ልጅ ኦንን ወሰዳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሌዊ ነገድ የሆነው የቀዓት ጐሣ የይስዓር ልጅ ቆሬ፥ ከሮቤል ነገድ የሆኑት የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን፥ የፋሌትም ልጅ ኦን ዐመፁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሌዊም ልጅ የቀዓት ልጅ የይስዓር ልጅ ቆሬ ከሮቤልም ልጆች የኤልያብ ልጆች ዳታንና አቤሮን የፋሌትም ልጅ ኦን በሙሴ ላይ ተነሡ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 16:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የና​ሱን ደጆች ሰብ​ሮ​አ​ልና፥ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪያ ቀጥ​ቅ​ጦ​አ​ልና።


እነ​ዚ​ህም እንደ ወገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌ​ዊም የሕ​ይ​ወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።


የቀ​ዓ​ትም ልጆች እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል ናቸው፤ የቀ​ዓ​ትም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው።


የይ​ስ​ዓ​ርም ልጆች ቆሬ፥ ናፌግ፥ ዝክሪ ናቸው።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፤ አም​ላክ እሆ​ና​ችሁ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።”


“አባ​ታ​ችን በም​ድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢ​አት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገን መካ​ከል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ዶ​ችም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ መካ​ከል ምድር አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ለእ​ነ​ር​ሱም የነ​በ​ራ​ቸ​ውን ሁሉ በዋ​ጠ​ቻ​ቸው በሮ​ቤል ልጅ በኤ​ል​ያብ ልጆች በዳ​ታ​ንና በአ​ቤ​ሮን ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፤


ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፤ ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፤ በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።