እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
ማቴዎስ 8:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፤ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆም፤ መላው የከተማ ነዋሪ ኢየሱስን ለመገናኘት ወጣ፤ ባዩትም ጊዜ አገራቸውን ለቅቆ እንዲሄድ ለመኑት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፤ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድ ለመኑት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የከተማው ሰዎች ሁሉ ኢየሱስን ለማየት ወጡ፤ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው ወጥቶ እንዲሄድላቸው ለመኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ከተማው ሁሉ ኢየሱስን ሊገናኝ ወጣ፥ ባዩትም ጊዜ ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት። |
እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን አይቶ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር በታች ሰገደና፥ “እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።
ጌታችን ኢየሱስንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገደለት፤ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያለም በታላቅ ቃል ጮኸ፤ እንዳያሠቃየውም ማለደው።
አሁንም አንሙት፤ ይህችም ታላቅ እሳት አታጥፋን፤ እኛ የአምላካችን የእግዚአብሔርን ድምፅ ዳግመኛ ብንሰማ እንሞታለን።
ሳሙኤልም እግዚአብሔር የተናገረውን አደረገ፤ ወደ ቤተ ልሔምም መጣ። የከተማውም ሽማግሌዎች በተገናኙት ጊዜ ደነገጡ፥ “ነቢይ! የመጣኸው ለሰላም ነውን?” አሉት።