Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 8:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገ​ደ​ለት፤ “የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያ​ለም በታ​ላቅ ቃል ጮኸ፤ እን​ዳ​ያ​ሠ​ቃ​የ​ውም ማለ​ደው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እየጮኸ ፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም፣ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፤ ከእኔ ምን አለህ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም፦ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ? እንዳታሰቃየኝ እለምንሃለሁ፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ኢየሱስን ባየ ጊዜ ጮኸ፤ በኢየሱስ ፊትም ወደቀና ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? እባክህ አታሠቃየኝ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ በታላቅ ድምፅም፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳትሣቀየኝ እለምንሃለሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 8:28
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆም “ኢየሱስ ሆይ! የእግዚአብሔር ልጅ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?” እያሉ ጮኹ።


እግዚአብሔር ኀጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥


ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።


ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።


እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣኑ እባብ ደራ​ጎን ላይ፥ በክ​ፉ​ውም እባብ ደራ​ጎን ላይ ልዩ፥ ታላ​ቅና ብርቱ ሰይ​ፍን ያመ​ጣል። በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያለ​ውን ዘንዶ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


ወደ ምድ​ርም በወ​ረዱ ጊዜ ጋኔን ያደ​ረ​በት ሰው ከከ​ተማ ወጥቶ ተገ​ና​ኘው፤ ልብ​ሱ​ንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመ​ቃ​ብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይ​ገ​ባም ነበር፤


ክፉ​ውን ጋኔን ከዚያ ሰው ላይ እን​ዲ​ወጣ ያዝ​ዘው ነበ​ርና፤ ዘወ​ት​ርም አእ​ም​ሮ​ዉን ያሳ​ጣው ነበ​ርና፤ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በእ​ግር ብረት አስ​ረው ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ እግር ብረ​ቱ​ንም ይሰ​ብር ነበር፤ ጋኔ​ኑም በም​ድረ በዳ ያዞ​ረው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች