እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
ማቴዎስ 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ “እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ መናፍስትን በቃኣሉ አወጣ፤ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ምሽት በአጋንንት የተያዙ ብዙ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም መናፍስትን በቃሉ አስወጣ፤ በሽተኞችንም ሁሉ ፈወሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደሩባቸው ብዙ ሰዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ መናፍስቶቹን ሁሉ በቃል አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመሸም ጊዜ ሰዎች በአጋንንት የተያዙ ብዙ በሽተኞችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም በቃሉ ርኩሳን መናፍስትን አስወጣ፤ በሽተኞችንም ሁሉ ፈወሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ መናፍስትን በቃኣሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። |
እርሱም፥ “አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም መልካምን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና” አለ።
እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።
ኢየሱስም ሕዝቡ እንደ ገና ሲራወጥ አይቶ ርኵሱን መንፈስ ገሠጸና “አንተ ድዳ ደንቆሮም መንፈስ፥ እኔ አዝሃለሁ፤ ከእርሱ ውጣ! ከእንግዲህም አትግባበት፤” አለው።
ፀሐይም በገባ ጊዜ ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸውን ድውያን ሁሉ አመጡለት፤ ከእነርሱም በእያንዳንዱ ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው።
ብዙ አጋንንትም፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ” እያሉና እየጮሁ ይወጡ ነበር፤ እርሱም ይገሥጻቸው ነበር፤ ክርስቶስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበርና እንዲናገሩ አይፈቅድላቸውም ነበር።
ጴጥሮስም አልፎ ሲሄድ ጥላው ያርፍባቸው ዘንድ ድውዮችን በአልጋና በቃሬዛ እያመጡ በአደባባይ ያስቀምጡአቸው ነበር፤