Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 4:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ልዩ ልዩ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድው​ያን ሁሉ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ላይ እጁን ጭኖ ፈወ​ሳ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ፀሓይ መጥለቂያ ላይም፣ የተለያየ ሕመም ያደረባቸውን ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ፀሐይም ስትጠልቅ ሰዎች በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙባቸውን ሕሙማን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ፀሐይ ስትጠልቅ ሰዎች በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙባቸውን ሕመምተኞች ሁሉ ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ፀሐይም በገባ ጊዜ በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙ በሽተኞችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡአቸው፤ እርሱም በእያንዳቸው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 4:40
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶችም ይሄዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮችም ይሰማሉ፤ ሙታንም ይነሣሉ፤


ኢየሱስም በሰማ ጊዜ ከዚያ ብቻውን ወደ ምድረ በዳ በታንኳ ፈቀቅ አለ፤ ሕዝቡም ሰምተው ከከተማዎቹ በእግር ተከተሉት።


ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ ስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር።


“ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት፤” ብሎ አጥብቆ ለመነው።


በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር፥ ተአምር ሊያደርግ ምንም አልቻለም።


ከል​ብሱ ዘር​ፍና ከመ​ጠ​ም​ጠ​ሚ​ያዉ ጫፍ ቈር​ጠው እየ​ወ​ሰዱ በድ​ው​ያኑ ላይ ያኖ​ሩት ነበር፤ እነ​ር​ሱም ይፈ​ወሱ ነበር፤ ክፉ​ዎች መና​ፍ​ስ​ትም ይወጡ ነበር።


ጴጥ​ሮ​ስም አልፎ ሲሄድ ጥላው ያር​ፍ​ባ​ቸው ዘንድ ድው​ዮ​ችን በአ​ል​ጋና በቃ​ሬዛ እያ​መጡ በአ​ደ​ባ​ባይ ያስ​ቀ​ም​ጡ​አ​ቸው ነበር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች