የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በት​ርም ቢሆን፥ ከረ​ጢ​ትም ቢሆን፥ እን​ጀ​ራም ቢሆን፥ ወር​ቅም ቢሆን፥ ሁለት ልብ​ስም ቢሆን ለመ​ን​ገድ ምንም አት​ያዙ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም አላቸው፤ “ለመንገዳችሁ በትር፣ ከረጢት፣ እንጀራ፣ ገንዘብ፣ ወይም ትርፍ እጀ ጠባብ መያዝ አትያዙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም አላቸው፦ “ለመንገድ ምንም አትያዙ፤ በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ እንጀራም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፤ ሁለት እጀ ጠባብም አይኑራችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲህም አላቸው፦ “ለመንገዳችሁ የሚሆን ምንም አትያዙ፤ በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ ስንቅም ቢሆን፥ ገንዘብም ቢሆን፥ ቅያሬ ልብስም እንኳ ቢሆን አትያዙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም አላቸው፦ በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ እንጀራም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን ለመንገድ ምንም አትያዙ፥ ሁለት እጀ ጠባብም አይሁንላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 9:3
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


ዐሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ ጠራ፤ ሁለት ሁለቱንም ይልካቸው ጀመር፤ በርኵሳን መናፍስትም ላይ ሥልጣን ሰጣቸው፤


ለደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ህ​ዋ​ለሁ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ስለ​ም​ት​በ​ሉ​ትና ስለ​ም​ት​ጠ​ጡት፥ ለሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁም ስለ​ም​ት​ለ​ብ​ሱት አት​ጨ​ነቁ።


እነሆ፥ ዛሬ ያለ​ውን፥ ነገም ወደ እሳት የሚ​ጣ​ለ​ውን የአ​በባ አገዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ከሆነ፥ እና​ንተ እም​ነት የጐ​ደ​ላ​ችሁ፥ ለእ​ና​ን​ተማ እን​ዴት አብ​ልጦ አያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ?


ደግ​ሞም፥ “ያለ ስልቻ፥ ያለ ከረ​ጢ​ትና ያለ ጫማ በላ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ በውኑ የተ​ቸ​ገ​ራ​ች​ሁት ነገር ነበ​ርን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “የለም” አሉት።


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሁለት ልብስ ያለው አን​ዱን ለሌ​ለው ይስጥ፤ ምግብ ያለ​ውም እን​ዲሁ ያድ​ርግ።”


ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደ​ረ​ገ​ለት፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ለምሳ ተቀ​ም​ጠው የነ​በሩ ቀራ​ጮ​ችና ኀጢ​አ​ተ​ኞች፥ ሌሎ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።


በም​ት​ገ​ቡ​በት ቤት በዚያ ተቀ​መጡ፤ እስ​ክ​ት​ሄ​ዱም ድረስ ከዚያ አት​ውጡ።


የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።