ሉቃስ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ስለ ተያዘው ዓሣ ተደንቀው ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያለው እርሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት በያዙት ዓሣ ብዛት ስለ ተደነቁ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ስላጠመዱት ዓሣ ተደንቀው ነበርና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያለበት ምክንያት እርሱና አብረውት የነበሩት ጓደኞቹ ሁሉ ከያዙት ዓሣ ብዛት የተነሣ እጅግ ተገርመው ስለ ነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስላጠመዱት ዓሣ እርሱ ከእርሱ ጋርም የነበሩ ሁሉ ተደንቀዋልና፥ |
ሁሉም ደነገጡ፤ እርስ በርሳቸውም ተነጋገሩ፤ እንዲህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምንድን ነው? ክፉዎችን አጋንንት በሥልጣንና በኀይል ያዝዛቸዋልና፥ እነርሱም ይወጣሉና።”
እንዲሁም የስምዖን ባልንጀራዎች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ተደነቁ፤ ጌታችን ኢየሱስም ስምዖንን፥ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህስ ሰውን ታጠምዳለህ” አለው።
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን አይቶ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር በታች ሰገደና፥ “እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።