የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 4:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥ​ተው ከከ​ተማ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ ገፍ​ተ​ውም ይጥ​ሉት ዘንድ ከተ​ማ​ቸው ተሠ​ር​ታ​ባት ወደ ነበ​ረች ተራራ ጫፍ ወሰ​ዱት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከተቀመጡበትም ተነሥተው ከከተማው አስወጡት፤ ቍልቍል ሊጥሉትም ከተማቸው ወደ ተሠራችበት ኰረብታ አፋፍ ወሰዱት፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ተነሥተውም ከከተማይቱ ውጭ አወጡት፤ ገፍትረውም ሊጥሉት ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ኮረብታ አፋፍ ላይ ወሰዱት፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ተነሥተውም ኢየሱስን ጐትተው ከከተማ ውጪ አወጡት፤ ወደ ገደልም ገፍትረው ሊጥሉት ፈልገው ከተማቸው ወደ ተሠራችበት ኰረብታ አፋፍ ላይ ወሰዱት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 4:29
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የይ​ሁ​ዳም ልጆች ደግሞ ዐሥር ሺህ ሰዎ​ችን ማረኩ። ወደ ዐለ​ቱም ራስ ላይ አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ከዐ​ለ​ቱም ራስ ላይ ጣሉ​አ​ቸው፤ ሁሉም ተፈ​ጠ​ፈጡ።


እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ሰው፥ በአ​ፉም መና​ገር እን​ደ​ማ​ይ​ችል ሰው ሆንሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ሰው​ዬው ይገ​ደል፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት” አለው።


በም​ኵ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ይህን ሰም​ተው ተቈጡ።


የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እንደ ሆና​ች​ሁስ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን ቃሌ በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ኖ​ር​ምና ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ።


አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን እው​ነት የም​ነ​ግ​ራ​ች​ሁን ሰው ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ፤ አብ​ር​ሃ​ምስ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም።


ሊደ​በ​ድ​ቡ​ትም ድን​ጋይ አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ተሰ​ወ​ራ​ቸው፤ ከቤተ መቅ​ደ​ስም ወጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አልፎ ሄደ።


ስለ​ዚ​ህም ኢየ​ሱስ ሕዝ​ቡን በደሙ ይቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ ከከ​ተማ ውጭ ተሰ​ቀለ።