የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፥ የመራዩት ልጅ፥ የሳዶቅ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ፤
ሉቃስ 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄዶም ከካህናት አለቆችና ከታላላቆች ጋር እርሱን አሳልፎ እንዲሰጣቸው ተነጋገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደሱ ሹሞች ሄዶ ኢየሱስን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ተነጋገረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከቤተ መቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደስ ዘብ አዛዦች ሄዶ ኢየሱስን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከመቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ። |
የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፥ የመራዩት ልጅ፥ የሳዶቅ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ፤
ጌታችን ኢየሱስም ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፥ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን እንዲህ አላቸው፥ “ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን?
ከዚህም በኋላ የቤተ መቅደሱ ሹም ከሎሌዎቹ ጋር ሔዶ አባብሎ አመጣቸው፤ በግድም አይደለም፤ በድንጋይ እንዳይደበድቧቸው ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።