Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 22:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊይ​ዙት ወደ እርሱ የመ​ጡ​ትን የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችን፥ የቤተ መቅ​ደስ ሹሞ​ች​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሌባን እን​ደ​ም​ት​ይዙ በሰ​ይ​ፍና በጎ​መድ ልት​ይ​ዙኝ መጣ​ች​ሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ከዚያም ኢየሱስ ሊይዙት የመጡትን የካህናት አለቆች፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችና ሽማግሌዎችን እንዲህ አላቸው፤ “ወንበዴ እንደሚይዝ ሰው፣ ሰይፍና ቈመጥ ይዛችሁ ወጣችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 ኢየሱስም ወደ እርሱ ለመጡበት ለካህናት አለቆችና ለቤተ መቅደስ አዛዦች ለሽማግሌዎችም “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ መጣችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ሊይዙት የመጡትን የካህናት አለቆች፥ የቤተ መቅደስ የዘብ አዛዦችንና የሕዝብ ሽማግሌዎችንም እንዲህ አላቸው፦ “እኔን እንደ ወንበዴ ልትይዙ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ መጣችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 ኢየሱስም ወደ እርሱ ለመጡበት ለካህናት አለቆችና ለመቅደስ አዛዦች ለሽማግሌዎችም፦ ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ወጣችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 22:52
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሄዶም ከካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ከታ​ላ​ላ​ቆች ጋር እር​ሱን አሳ​ልፎ እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው ተነ​ጋ​ገረ።


ከዚ​ህም በኋላ የቤተ መቅ​ደሱ ሹም ከሎ​ሌ​ዎቹ ጋር ሔዶ አባ​ብሎ አመ​ጣ​ቸው፤ በግ​ድም አይ​ደ​ለም፤ በድ​ን​ጋይ እን​ዳ​ይ​ደ​በ​ድ​ቧ​ቸው ሕዝ​ቡን ይፈሩ ነበ​ርና።


እኔ በዓ​ለም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለሁ ግን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን በስ​ምህ እጠ​ብ​ቃ​ቸው ነበር፤ ጠበ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም፤ የመ​ጽ​ሐ​ፉም ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ከጥ​ፋት ልጅ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ስን​ኳን አል​ጠ​ፋም።


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


ካህ​ኑም ዮዳሄ በጭ​ፍ​ራው ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን የመቶ አለ​ቆች፥ “ወደ ሰልፉ መካ​ከል አው​ጡ​አት፤ የሚ​ከ​ተ​ላ​ት​ንም በሰ​ይፍ ግደ​ሉት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፤ ካህኑ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አት​ገ​ደል” ብሎ​አ​ልና።


ይህንም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ተቈ​ጠረ ተብሎ የተ​ጻ​ፈው በእኔ ይደ​ር​ሳል፤ ስለ እኔ የተ​ጻ​ፈ​ውም ሁሉ ይፈ​ጸ​ማል።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ​ንስ ተው” አለ፤ ወዲ​ያ​ውም ጆሮ​ውን ዳስሶ አዳ​ነው።


ዘወ​ት​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር በቤተ መቅ​ደስ ስኖር እጃ​ች​ሁን እንኳ አል​ዘ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብ​ኝም፤ ነገር ግን ጊዜ​ያ​ችሁ ይህ ነው፤ የጨ​ለ​ማው አበ​ጋ​ዝም ሥል​ጣኑ ይህ ነው።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች