የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቄሬ​ኔ​ዎስ ለሶ​ርያ መስ​ፍን በነ​በረ ጊዜ ይህ የመ​ጀ​መ​ርያ ቈጠራ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህም ቄሬኔዎስ የሶርያ ገዥ በነበረበት ጊዜ የተደረገ የመጀመሪያው የሕዝብ ቈጠራ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቄሬኔዎስ የሶርያ አገረ ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያው ምዝገባ ተከናወነ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህም የመጀመሪያው የሕዝብ ቈጠራ በተደረገ ጊዜ ቄሬኔዎስ የሶርያ አገረ ገዥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 2:2
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው ሁሉ ይቈ​ጠር ዘንድ ከአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ቄሣር ትእ​ዛዝ ወጣ።


ሰው ሁሉ ሊቈ​ጠር ወደ​የ​ከ​ተ​ማው ሄደ።


ጢባ​ር​ዮስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስት ዓመት ጴን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ የይ​ሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮ​ድ​ስም በገ​ሊላ የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወን​ድሙ ፊል​ጶ​ስም የኢ​ጡ​ር​ያ​ስና የጥ​ራ​ኮ​ኒ​ዶስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳ​ን​ዮ​ስም የሳ​ብ​ላ​ኒስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥


እር​ሱም ብልህ ሰው በሆነ ሰር​ግ​ዮስ ጳው​ሎስ በሚ​ባል አገረ ገዢ ዘንድ ይኖር ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ሊሰማ ወድዶ በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን ወደ እርሱ ጠራ​ቸው።


ጋል​ዮ​ስም የአ​ካ​ይያ አገረ ገዢ በሆነ ጊዜ አይ​ሁድ ተባ​ብ​ረው በጳ​ው​ሎስ ላይ ተነሡ፤ ወደ ሸን​ጎም አመ​ጡት።


“ከሉ​ስ​ዮስ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ፥ ለክ​ቡር አገረ ገዢ ፊል​ክስ፥ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን።


ከዚ​ህም በኋላ ንጉሡ፥ ሀገረ ገዥ​ውም፥ በር​ኒ​ቄም፥ ሹሞ​ቻ​ቸ​ውም ተነሡ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ ሰዎች ለግ​ብር በተ​ቈ​ጠ​ሩ​በት ወራት ገሊ​ላ​ዊው ይሁዳ ተነሣ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ተከ​ተ​ሉት፤ እር​ሱም ሞተ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​ትም ሁሉ ተበ​ታ​ተኑ።