የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሉቃስ 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቤት ተቀ​መጡ፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ገ​ኘ​ው​ንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠ​ራ​ተኛ ዋጋው ይገ​ባ​ዋ​ልና፤ ከቤ​ትም ወደ ቤት አት​ሂዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያቀረቡላችሁን ሁሉ እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያ ቤት ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል። ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋልና እነርሱ የሚሰጡአችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ተቀመጡ። ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለሠራተኛ ደመወዝ ይገባዋል፤ ስለዚህ በገባችሁበት ቤት ያቀረቡላችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ ቈዩ፤ ከቤት ወደ ቤትም አትዘዋወሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ቤት ከእነርሱ ዘንድ ካለው እየበላችሁና እየጠጣችሁ ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሉቃስ 10:7
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ን​ተም ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁም፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ የማ​ገ​ል​ገ​ላ​ችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።


“በማናቸውም ስፍራ ወደ ቤት ብትገቡ ከዚያ እስክትወጡ ድረስ በዚያው ተቀመጡ።


በዚ​ያም የሰ​ላም ልጅ ቢኖር ሰላ​ማ​ችሁ ያድ​ር​በ​ታል፤ ያለ​ዚያ ግን ሰላ​ማ​ችሁ ይመ​ለ​ስ​ላ​ች​ኋል።


በም​ት​ገ​ቡ​በት ቤት በዚያ ተቀ​መጡ፤ እስ​ክ​ት​ሄ​ዱም ድረስ ከዚያ አት​ውጡ።


እር​ስ​ዋም ከቤተ ሰቦ​ችዋ ጋር ተጠ​መ​ቀች፤ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አማኝ ካደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ኝስ ወደ ቤቴ ገብ​ታ​ችሁ እደሩ” ብላ ማለ​ደ​ችን፤ የግ​ድም አለ​ችን።


ወደ ቤቱም አግ​ብቶ ማዕድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ በጌ​ታ​ችን ስለ አመ​ነም እርሱ ከቤተ ሰቡ ጋር ደስ አለው።


ከወ​ኅኒ ቤቱም ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ገብ​ተው ወን​ድ​ሞ​ችን አገኙ፤ አጽ​ና​ን​ተ​ዋ​ቸ​ውም ሔዱ።


ይህ​ንም ነገር ንኡሰ ክር​ስ​ቲ​ያን ይስ​ማው፤ መል​ካ​ሙ​ንም ነገር ሁሉ ከሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው ይማር።


እና​ን​ተም፥ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ች​ሁም፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት ስለ​ሌ​ለው በደ​ጆ​ቻ​ችሁ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጠው ሌዋ​ዊም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ከአ​ባ​ቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ከመ​ብል ድር​ሻ​ውን ይወ​ስ​ዳል።


ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፤ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።


የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።