Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 10:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ለሠራተኛ ደመወዝ ይገባዋል፤ ስለዚህ በገባችሁበት ቤት ያቀረቡላችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ ቈዩ፤ ከቤት ወደ ቤትም አትዘዋወሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ያቀረቡላችሁን ሁሉ እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያ ቤት ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል። ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋልና እነርሱ የሚሰጡአችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ተቀመጡ። ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በዚ​ያም ቤት ተቀ​መጡ፤ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ገ​ኘ​ው​ንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠ​ራ​ተኛ ዋጋው ይገ​ባ​ዋ​ልና፤ ከቤ​ትም ወደ ቤት አት​ሂዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በዚያም ቤት ከእነርሱ ዘንድ ካለው እየበላችሁና እየጠጣችሁ ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋልና። ከቤት ወደ ቤት አትተላለፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 10:7
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለምትሰጡት አገልግሎት የድካም ዋጋችሁ ስለ ሆነ የተረፈውንም እናንተና ቤተሰቦቻችሁ በየትኛውም ስፍራ ሆናችሁ መመገብ ትችላላችሁ፤


በማናቸውም ስፍራ ወደ አንድ ሰው ቤት ስትገቡ፥ ያንን ስፍራ እስክትለቁ ድረስ በዚያው ቈዩ፤


ሰላም ወዳድ ሰው በዚያ ቤት ቢኖር ሰላማችሁ ያድርበታል፤ አለበለዚያ ግን ሰላማችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል።


በእንግድነት በምትገቡበት ቤት ሁሉ ከዚያ መንደር ወጥታችሁ እስክትሄዱ ድረስ በዚያው ቈዩ።


እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።


ከዚህ በኋላ ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ቤቱ ወስዶ ምግብ አቀረበላቸው፤ በእግዚአብሔር ስላመነም ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር ደስ አለው።


ጳውሎስና ሲላስም ከወህኒ ቤት ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፤ እዚያም ወንድሞችን አግኝተው፥ አጽናኑአቸውና ከተማውን ለቀው ሄዱ።


ቃሉን የሚማር ሰው ከአስተማሪው ጋር መልካሙን ነገር ሁሉ ይካፈል።


እናንተ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆቻችሁ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም ከእናንተ ጋር የርስት ክፍያ ከሌላቸው በከተሞቻችሁ ከሚኖሩ ከሌዋውያን ጋር በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ትደሰታላችሁ።


ከቤተሰብ ንብረት ሽያጭ ገንዘብ የሚቀበል ቢሆንም እንኳ እርሱም ሌሎቹ ካህናት በሚያገኙት መጠን ድርሻውን ይቀበላል።


ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።


በሥራ የሚደክም ገበሬ ከሥራው ከሚገኘው ፍሬ የመጀመሪያውን ማግኘት ይገባዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች