ኢያሱ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ሁሉ ሠራዊቶቻቸውን በከተማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳርቻውም እስከ ከተማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከከተማዪቱ በስተሰሜን የነበሩትንም፣ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ የሸመቁትንም ወታደሮች ሁሉ ስፍራ ስፍራቸውን እንዲይዙ አደረጋቸው፤ በዚያችም ሌሊት ኢያሱ ወደ ሸለቆው ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የኋላ ደጀን የሆነውን ሕዝብ አኖሩ፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው ውስጥ አደረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ዋናውን ሠራዊት ከከተማ በስተሰሜን በኩል፥ የኋላውን ደጀን በስተምዕራብ በኩል አሰለፉ፤ ኢያሱ ግን ሌሊቱን በሸለቆው አሳለፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የተደበቁትን ሕዝብ አኖሩ፥ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ። |
የጋይም ንጉሥ በሰማ ጊዜ ፈጥኖ ሄደ። የከተማዪቱም ሰዎች ወጡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ በዓረባ ፊት ባለው አንድ ስፍራ እስራኤልን በጦርነት ተቀበሉአቸው፤ እርሱ ግን ከከተማዪቱ በስተኋላ እንደ ተደበቁ አያውቅም ነበር።