Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከከተማዪቱ በስተሰሜን የነበሩትንም፣ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ የሸመቁትንም ወታደሮች ሁሉ ስፍራ ስፍራቸውን እንዲይዙ አደረጋቸው፤ በዚያችም ሌሊት ኢያሱ ወደ ሸለቆው ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የኋላ ደጀን የሆነውን ሕዝብ አኖሩ፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው ውስጥ አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እነርሱም ዋናውን ሠራዊት ከከተማ በስተሰሜን በኩል፥ የኋላውን ደጀን በስተምዕራብ በኩል አሰለፉ፤ ኢያሱ ግን ሌሊቱን በሸለቆው አሳለፈ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሕዝ​ቡም ሁሉ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በከ​ተ​ማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ከተ​ማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያ​ሱም በዚ​ያች ሌሊት ወደ ሸለ​ቆው መካ​ከል ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የተደበቁትን ሕዝብ አኖሩ፥ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:13
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢያሱ ቀደም ብሎ ዐምስት ሺሕ ሰው ያህል በመውሰድ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ፣ በቤቴልና በጋይ መካከል እንዲያደፍጡ አድርጎ ነበር።


ከተማዪቱን ስትይዙም በእሳት አቃጥሏት፤ እግዚአብሔር ያዘዘውንም አድርጉ፤ እነሆ አዝዣችኋለሁ።”


የጋይ ንጉሥ ይህን ባየ ጊዜ እርሱና የከተማዪቱ ወንዶች ሁሉ ማልደው በመገሥገሥ፣ እስራኤልን ለመውጋት ከዓረባ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ስፍራ መጡ፤ ንጉሡ ግን ከከተማዪቱ በስተጀርባ ያደፈጠ ኀይል የሚጠባበቀው መሆኑን አያውቅም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች