ኢያሱ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም አላቸው፥ “በእኔና በእግዚአብሔር ፊት ወደ ዮርዳኖስ መካከል ዕለፉ፤ እያንዳንዱ ሰው በዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላቸው፤ “ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድማችሁ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዕለፉ፤ እያንዳንዳችሁም በእስራኤል ነገድ ቍጥር አንዳንድ ድንጋይ በትከሻችሁ ተሸከሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “በአምላካችሁ በጌታ ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል እለፉ፤ ከእናንተም ሰው ሁሉ በእስራኤል ልጆች ነገድ ቍጥር በትከሻው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቀድማችሁ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ውረዱ፤ በእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ ስም፥ እያንዳንዳችሁ አንዳንድ ድንጋይ በማንሣት በትከሻችሁ ተሸከሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም አላቸው፦ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ወደ ዮርዳኖስ መካከል እለፉ፥ ከእናንተም ሰው ሁሉ በእስራኤል ልጆች ነገድ ቁጥር በጫንቃው ላይ አንድ አንድ ድንጋይ ከዚያ ይሸከም። |
ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ፤ ማለዳም ተነሣ፤ ከተራራውም በታች መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለትም ድንጋዮችን ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ አቆመ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ታላላቅ ድንጋዮችን ለእናንተ አቁሙ፤ በኖራም ምረጓቸው።
“እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ የቅጽራቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚደርስ ታላላቆች ከተሞችን ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገረዋለህ።
በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም ወደ ገለዓድ በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዮርዳኖስ አጠገብ የሚታይ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ።
እነዚህም ምልክት ይሆኑላችኋል፤ ልጅህ ነገ፦ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥ ልጅህን እንዲህ ትለዋለህ፦