የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 23:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያሱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ሹሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ እነሆ ሸም​ግ​ያ​ለሁ፤ ዘመ​ኔም አል​ፎ​አል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢያሱ እስራኤልን ሁሉ አለቆቻቸውን፣ መሪዎቻቸውን፣ ፈራጆቻቸውንና ሹማምታቸውን በሙሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ አርጅቻለሁ፤ ዕድሜዬም ገፍቷል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱ እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውንም አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምንቶቻቸውንም ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ሸምግያለሁ፥ ዕድሜዬም ገፍቷል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም እርሱ መላውን እስራኤልን፥ ሽማግሌዎችን፥ መሪዎችን፥ ዳኞችንና የጦር አዛዦችን በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ እኔ በዕድሜ ሸምግያለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱ እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውንም አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምቶቻቸውንም ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እኔ ሸምግያለሁ፥ በዕድሜም አርጅቻለሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 23:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡ ዳዊ​ትም አረጀ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ ልብ​ስም ይደ​ር​ቡ​ለት ነበር፤ ነገር ግን አይ​ሞ​ቀ​ውም ነበር።


ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤተ መን​ግ​ሥት ሠርቶ ከፈ​ጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ንጉሡ ሰሎ​ሞን በጽ​ዮን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አለ​ቆች ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱ​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ሰበ​ሰበ።


በወ​ይ​ንም ቦታ​ዎች ላይ ራማ​ታ​ዊው ሰሜኢ ሹም ነበረ፤ ለወ​ይ​ንም ጠጅ ዕቃ ቤት በሚ​ሆ​ነው በወ​ይኑ ሰብል ላይ የሳ​ፍ​ኒው ዘብዲ ሹም ነበረ።


ዳዊ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አለ​ቆች ሁሉና የፍ​ርድ አለ​ቆ​ችን፥ ንጉ​ሡ​ንም በየ​ተራ የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ትን አለ​ቆ​ቹን፥ ሻለ​ቆ​ቹ​ንም፥ የመቶ አለ​ቆ​ቹ​ንም፥ በን​ጉ​ሡና በል​ጆቹ ሀብ​ትና ንብ​ረት ላይ፥ መባ ባለ​በት ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንም፥ ኀያ​ላ​ኑ​ንና ሰል​ፈ​ኞ​ቹን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


ይህን ቃል በጆ​ሮ​አ​ቸው እነ​ግር ዘንድ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንም አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸው ዘንድ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ች​ሁን አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ፥ ሹሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ጻፎ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሰብ​ስ​ቡ​ልኝ፤


ኢያ​ሱም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ ዘመ​ንህ አለፈ፤ ያል​ተ​ወ​ረ​ሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀር​ታ​ለች፤


እና​ን​ተም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ስለ እና​ንተ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ስለ እና​ንተ የተ​ዋጋ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠራ​ቸው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አቆ​ማ​ቸው።


አሁ​ንም እነሆ፥ ንጉሡ በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳል፤ እኔም አር​ጅ​ቻ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲ​ህም አር​ፋ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ልጆቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ እኔም ከሕ​ፃ​ን​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በፊ​ታ​ችሁ ሄድሁ።