እንዲህም ሆነ፤ ከሦስት ወር በኋላ ለይሁዳ፥ “ምራትህ ትዕማር ሴሰነች፤ እነሆ፥ በዝሙት ፀነሰች” ብለው ነገሩት። ይሁዳም፥ “አውጡአትና በእሳት ትቃጠል” አለ።
ኢያሱ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢያሪኮም ንጉሥ፥ “ሀገራችንን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን በዚችም ሌሊት ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጪ በሉአት” ብሎ ወደ ረዓብ ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢያሪኮም ንጉሥ፣ “ወደ አንቺ መጥተው ወደ ቤትሽ የገቡት ሰዎች ምድሪቱን በሙሉ ለመሰለል ስለ ሆነ፣ እንድታስወጪአቸው” የሚል መልእክት ወደ ረዓብ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ፦ “አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የኢያሪኮ ንጉሥ “ምድሪቱን ሊሰልሉ የመጡ ስለ ሆኑ ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጥተሽ አስረክቢ!” ብሎ ወደ ረዓብ ትእዛዝ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢያሪኮም ንጉሥ፦ አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ። |
እንዲህም ሆነ፤ ከሦስት ወር በኋላ ለይሁዳ፥ “ምራትህ ትዕማር ሴሰነች፤ እነሆ፥ በዝሙት ፀነሰች” ብለው ነገሩት። ይሁዳም፥ “አውጡአትና በእሳት ትቃጠል” አለ።
የአሞንም ልጆች አለቆች ጌታቸውን ሐኖንን፥ “ዳዊት አባትህን በፊትህ ለማክበር አጽናኞችን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ዳዊትስ ከተማዪቱን ለመመርመርና ለመሰለል፥ ለመፈተንም አገልጋዮቹን የላከ አይደለምን?” አሉት።
የአቤሴሎምም አገልጋዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፥ “አኪማሆስና ዮናታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲቱም፥ “ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ፤ ጥቂትም ቀደሙአችሁ” አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው አጡአቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ።
የአሞን ልጆች አለቆች ግን ሐናንን፥ “ዳዊት የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ አባትህን በማክበር ነውን? አገልጋዮቹስ ከተማዪቱን ለመመርመርና ሀገሪቱንም ለመሰለል ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?” አሉት።
“ተሳዳቢውን ከሰፈር ወደ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት።”
ጲላጦስም እንደገና ወደ ውጭ ወጣና፥ “እነሆ፥ በእርሱ ላይ አንዲት በደል ስንኳን ያገኘሁበት እንደሌለ ታውቁ ዘንድ ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ” አላቸው።
ይዞም ወኅኒ ቤት አስገባው፤ ለሚጠብቁት ለዐሥራ ስድስቱ ወታደሮችም አሳልፎ ሰጠው፤ ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ሊያቀርበው ወድዶ ነበር።
ሄሮድስም ማለዳ ያቀርበው ዘንድ በወደደባት በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ ሁለቱን እጆቹን በሰንሰለት ታስሮ በሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም የወኅኒ ቤቱን በር ይጠብቁ ነበር።
እንዲህም አደረጉ፤ አምስቱንም ነገሥት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንንም ንጉሥ፥ የየርሙትንም ንጉሥ፥ የላኪስንም ንጉሥ፥ የአዶላምንም ንጉሥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው።