Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ፦ “አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የኢያሪኮም ንጉሥ፣ “ወደ አንቺ መጥተው ወደ ቤትሽ የገቡት ሰዎች ምድሪቱን በሙሉ ለመሰለል ስለ ሆነ፣ እንድታስወጪአቸው” የሚል መልእክት ወደ ረዓብ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከዚህ በኋላ የኢያሪኮ ንጉሥ “ምድሪቱን ሊሰልሉ የመጡ ስለ ሆኑ ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጥተሽ አስረክቢ!” ብሎ ወደ ረዓብ ትእዛዝ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ፥ “ሀገ​ራ​ች​ንን ሁሉ ሊሰ​ልሉ መጥ​ተ​ዋ​ልና ወደ አንቺ የመ​ጡ​ትን በዚ​ችም ሌሊት ወደ ቤትሽ የገ​ቡ​ትን ሰዎች አውጪ በሉ​አት” ብሎ ወደ ረዓብ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የኢያሪኮም ንጉሥ፦ አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 2:3
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።


እኛ ግን እንዲህ አልነው፤ ‘እኛ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።


የአሞናውያን መኳንንት፥ ጌታቸው ሐኑንን፥ “ዳዊት የተሰማውን ኀዘን ለመግለጽ ሰዎች መላኩ አባትህን ለማክበር አስቦ ይመስልሃል? የላካቸው ሰዎች ከተማዪቱን እንዲመረምሩ፥ እንዲሰልሉና እንዲያጠፏት አይደለምን?” አሉት።


የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፥ “አሒማዓጽና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቋት። ሴቲቱም፥ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፥ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


የአሞን ልጆች ሹማምንት ግን ሐኖንን እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት አባትህን አክብሮ የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ባርያዎቹስ አገሪቱን ለመመርመር፥ ለማጥፋት፥ ለመሰለልም ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?”


ክፉ ሰው በመቅሠፍት ቀን እንደሚተርፍ፥ በቁጣው ቀን እንደሚድን።


“ተሳዳቢውን ከሰፈሩ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገረው።


ጲላጦስም በድጋሚ ወደ ውጭ ወጥቶ “እነሆ፥ አንዲት በደል እንኳን እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ” አላቸው።


በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው፤ ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው።


ሄሮድስም ሊያወጣው ባሰበ ጊዜ፥ በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ከሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ሆነው ወኅኒውን ይጠብቁ ነበር።


እንዲህም አደረጉ፤ አምስቱንም ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ የኬብሮንንም ንጉሥ የየርሙትንም ንጉሥ የለኪሶንም ንጉሥ የዔግሎምንም ንጉሥ፥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው።


ለኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ።”


ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸገቻቸው፤ እርሷም እንዲህ አለች፦ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ከወዴት እንደ ሆኑ ግን አላወቅሁም፤


እርሱም፥ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፤ ማንም ሰው መጥቶ፥ ‘እዚህ ሰው አለ?’ ቢልሽ፥ ‘የለም በይ’” አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች