ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤቶሮን ዳርቻ ድረስ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
ኢያሱ 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበራቸውም በደቡብ በኩል ወዳለው ወደ ቃራና ሸለቆና ወደ ኢያሪያል ሸለቆ ይወርዳል፤ የኤፍሬም ዕጣ የሆነው ጤሬሜንቶስ የሚባለው ዛፍም በምናሴ ከተሞች መካከል አለ፤ የምናሴም ድንበር በሰሜን በኩል ወደ ወንዙ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በመቀጠል ድንበሩ በደቡብ በኩል ወደ ቃና ወንዝ ይደርሳል። በምናሴ ከተሞችም መካከል የኤፍሬም ከተሞች ነበሩ፤ ያም ሆኖ የምናሴ ድንበር የወንዙ ሰሜናዊ ክፍል ሲሆን፣ እስከ ባሕሩ ይዘልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ቃና ወንዝ ወረደ፤ በምናሴም ከተሞች መካከል ከወንዙ በደቡብ በኩል የሚገኙት እነዚህ ከተሞች ለኤፍሬም ሆኑ፤ የምናሴም ድንበር በወንዙ በኩል በሰሜን ወገን ነበረ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንበሩም ከዚያ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርሳል፤ ከወንዙ በስተ ደቡብ የሚገኙት ከተሞች ምንም እንኳ በምናሴ ግዛት ክልል ውስጥ ቢሆኑ የኤፍሬም ይዞታዎች ነበሩ፤ የምናሴ ድንበር በሰሜን በኩል ከወንዙ እየተዋሰነ መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ወደ ቃና ወንዝ ከወንዙ በደቡብ ወገን ወረደ፥ በምናሴም ከተሞች መካከል የነበሩት እነዚህ ከተሞች ለኤፍሬም ሆኑ፥ የምናሴም ድንበር በወንዙ በኩል በሰሜን ወገን ነበረ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። |
ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤቶሮን ዳርቻ ድረስ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፤ በሰሜን በኩል ያለውም ለምናሴ ነበረ፤ ድንበሩም ባሕር ነበረ፤ በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅም በኩል ወደ ይሳኮር ይደርሳል።
ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ መስፋጥ ምንጭ ወደ ጢሮስ ይዞራል፤ ድንበሩም ወደ ኢያሴፍ ይዞራል፤ መውጫውም በሌብና በኮዛብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤