Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 17:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም በመቀጠል ድንበሩ በደቡብ በኩል ወደ ቃና ወንዝ ይደርሳል። በምናሴ ከተሞችም መካከል የኤፍሬም ከተሞች ነበሩ፤ ያም ሆኖ የምናሴ ድንበር የወንዙ ሰሜናዊ ክፍል ሲሆን፣ እስከ ባሕሩ ይዘልቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ድንበሩም ወደ ቃና ወንዝ ወረደ፤ በምናሴም ከተሞች መካከል ከወንዙ በደቡብ በኩል የሚገኙት እነዚህ ከተሞች ለኤፍሬም ሆኑ፤ የምናሴም ድንበር በወንዙ በኩል በሰሜን ወገን ነበረ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ድንበሩም ከዚያ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርሳል፤ ከወንዙ በስተ ደቡብ የሚገኙት ከተሞች ምንም እንኳ በምናሴ ግዛት ክልል ውስጥ ቢሆኑ የኤፍሬም ይዞታዎች ነበሩ፤ የምናሴ ድንበር በሰሜን በኩል ከወንዙ እየተዋሰነ መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በደ​ቡብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ቃራና ሸለ​ቆና ወደ ኢያ​ሪ​ያል ሸለቆ ይወ​ር​ዳል፤ የኤ​ፍ​ሬም ዕጣ የሆ​ነው ጤሬ​ሜ​ን​ቶስ የሚ​ባ​ለው ዛፍም በም​ናሴ ከተ​ሞች መካ​ከል አለ፤ የም​ና​ሴም ድን​በር በሰ​ሜን በኩል ወደ ወንዙ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ድንበሩም ወደ ቃና ወንዝ ከወንዙ በደቡብ ወገን ወረደ፥ በምናሴም ከተሞች መካከል የነበሩት እነዚህ ከተሞች ለኤፍሬም ሆኑ፥ የምናሴም ድንበር በወንዙ በኩል በሰሜን ወገን ነበረ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 17:9
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያም በምዕራብ በኩል ቍልቍል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል።


በደቡብ በኩል ያለው ምድር የኤፍሬም ሲሆን፣ በሰሜን በኩል ያለው ደግሞ የምናሴ ነበር፤ የምናሴ ግዛት እስከ ባሕሩ የሚደርስ ሲሆን፣ ሰሜናዊ ድንበሩ አሴር፣ ምሥራቃዊ ድንበሩ ደግሞ ይሳኮር ነው።


ድንበሩ ወደ ራማ ከዞረ በኋላ ወደ ተመሸገው ወደ ጢሮስ ከተማ ታጥፎ ወደ ሖሳ ይመለስና በአክዚብ በኩል ሜድትራኒያን ባሕር ደርሶ ይቆማል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች