የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዕጣ​ቸ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከአ​ለው ከገ​ለ​ዓ​ድና ከባ​ሳን ሀገር በቀር ለም​ናሴ ዐሥር ዕጣ ሆነ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምናሴም ከገለዓድና ከባሳን ምድር ሌላ፣ ዐሥር ቦታ የሚደለደል የመሬት ክፍል በዮርዳኖስ ምሥራቅ ነበረው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዮርዳኖስ ማዶ ካለው ከገለዓድና ከባሳን አገር ሌላ ለምናሴ ዐሥር ዕጣ ደረሰው፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምናሴ በዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ከሚገኙት ከገለዓድና ከባሳን ጋር በተጨማሪ ዐሥር ዕጣ እንዲደርሰው ተደርጎአል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዮርዳኖስ ማዶ ካለው ከገለዓድና ከባሳን አገር ሌላ ለምናሴ አሥር ዕጣ ሆነ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 17:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከን​ፍ​ታ​ሌም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለም​ናሴ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


ገለ​ዓ​ድ​ንም፥ የጌ​ሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ን​ንና የመ​ከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአ​ር​ሞ​ን​ዔ​ም​ንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥


የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ኢያ​ሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስን​ሆን እስከ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ባረ​ከን ለምን አንድ ክፍል፥ አን​ድም ዕጣ ብቻ ርስት አድ​ር​ገህ ሰጠ​ኸን?” ብለው ወቀ​ሱት።


እነ​ር​ሱም ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛ​ርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለ​ቆ​ችም ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን መካ​ከል ርስት እን​ዲ​ሰ​ጠን በሙሴ እጅ አዘዘ” አሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ከአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች ጋር ርስት ሰጣ​ቸው።


የም​ናሴ ሴቶች ልጆች በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ የገ​ለ​ዓ​ድም ምድር ለቀ​ሩት ለም​ናሴ ልጆች ሆኖ​አ​ልና።


ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ሙሴ በባ​ሳን ውስጥ ርስት ሰጥ​ቶ​አ​ቸው ነበር፤ ለቀ​ረው ለእ​ኩ​ሌ​ታው ግን ኢያሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል ርስት ሰጣ​ቸው። ኢያ​ሱም ወደ ቤታ​ቸው በአ​ሰ​ና​በ​ታ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ ብሎ መረ​ቃ​ቸው፦