ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞም ሴኬምና መንደሮችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፤
ኢያሱ 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኢያኖክም ወደ መአኮና፥ ወደ አጣሮትም፥ ወደ መንደሮቻቸውም ያልፋል፤ ወደ ኢያሪኮም ይገባል፥ ወደ ዮርዳኖስም ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢያኖክም በመነሣት ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ቍልቍል ይወርድና በኢያሪኮ በኩል አድርጎ ዮርዳኖስ ላይ ብቅ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ መጨረሻውም ዮርዳኖስ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያኖሐም ተነሥቶ ወደ ዐጣሮትና ወደ ናዓራት በመዘቅዘቅ ኢያሪኮ ደርሶ መመለሻው የዮርዳኖስ ወንዝ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፥ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ። |
ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞም ሴኬምና መንደሮችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፤
ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አካስሞን በቴርማ ሰሜን ያልፋል፤ ወደ ምሥራቅም ወደ ቲናስና ሴላስ ይዞራል፥ ከምሥራቅም ወደ ኢያኖክ ያልፋል።
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀርያትያርም አውራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።
በዚያችም ቀን ኢያሱ፥ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረቷን በበኵር ልጁ የሚጥል፥ በሮችዋንም በታናሹ ልጁ የሚያቆም ርጉም ይሁን” ብሎ ማለ።