ኢያሱ 15:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሴያዶት መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም፥ ጋዛም መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕርም ወሰኑ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሽዶድ በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮች ጋራ፣ ጋዛ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ጠረፍ በመለስ ካሉት ሰፈሮቿና መንደሮቿ ጋራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብጽ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በግብጽ ወሰን እስከሚገኘው ወንዝና እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ ድረስ የሚደርሱ ታናናሽ ከተሞችና መንደሮች ያሉአቸው አሽዶድና ጋዛ ተብለው የሚጠሩ ከተሞች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ። |
ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፤ የጌትን ቅጥር፥ የኢያቢስንም ቅጥር፥ የአዛጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም ሀገር ከተሞችን ሠራ።
ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አሰፋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከአንተም አስወጣቸዋለሁ።
የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው፥ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ።”
እስከ ጋዛም ድረስ በአሴሮት ተቀምጠው የነበሩትን ኤዋውያንንና ከቀጰዶቅያ የወጡ ቀጰዶቃውያንን አጠፉአቸው፤ በእነርሱም ፋንታ ተቀመጡ።
በግብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአምስቱ የፍልስጥኤም ግዛቶች ለጋዛ፥ ለአዛጦን፥ ለአስቀሎና፥ ለጌት፥ ለአቃሮን፥ እንዲሁም ለኤዌዎናውያን በተቈጠረችው በከነዓን ግራ በኩል እስካለችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤
ወደ አጽሞንም ያልፋል፤ በግብፅም ሸለቆ በኩል ይወጣል፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው።