በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤
ኢያሱ 15:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዶር፥ በጋድያል፥ ኖማን፥ መቄዶም፥ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግዴሮት፣ ቤትዳጎን፣ ናዕማና መቄዳ ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ስድስት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማና ማቄዳ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል። |
በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤
ደግሞም ፍልስጥኤማውያን በቆላውና በደቡብ በኩል ባሉት በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ጋቤሮትንም፥ ሠካዕንና መንደሮችዋን፥ ቴምናንና መንደሮችዋንም፥ ጋማዚእንና መንደሮችዋን ወስደው በዚያ ተቀምጠው ነበር።
ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየሀገራቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ፥ አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊጐበኙትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ መጡ።
ሕዝቡ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ በደኅና ተመለሱ፤ በእስራኤል ልጆች ላይ ምላሱን ማንቀሳቀስ የደፈረ ማንም ሰው የለም።
በዚያም ቀን መቄዳን ያዟት፤ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀሩም፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረጉ በመቄዳ ንጉሥ አደረጉ።
ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ቤቴጌነት ይዞራል፤ በመስዕም በኩል ከዛብሎንና ከጋይ ከይፍታሕኤል ይያያዛል ወደ ሳፍቱ ቤታሜሕና ወደ ኢንሂል ይደርሳል፤ ወደ ኮባ ማሾሜልም ያልፋል፤