ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እንዲህ ሲል፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አደረገኝ፤”
ኢያሱ 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንስሶቻቸው ከሚሆን ማሰማሪያቸውና ከእንስሶቻቸውም በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ሆነው ነበርና፤ ለሌዋውያኑ ግን ከሚኖሩባቸው ከተሞች እንዲሁም ለበግ፣ ለፍየልና ለከብት መንጎቻቸው መሰማሪያ እንዲሆን ዐብሮ የተከለለላቸውን ምድር ብቻ እንጂ ሌላ አልሰጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን ማሰማርያ በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም በምድሪቱ ለመኖሪያቸው የሚሆኑ ከተሞችና ለከብቶቻቸው ማሰማሪያ የሚሆን መሬት በቀር የርስት ድርሻ አልተሰጣቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፥ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። |
ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እንዲህ ሲል፥ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አደረገኝ፤”
ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ምናሴና ኤፍሬም ናቸው። ሶርያዊት ዕቅብቱ የወለደችለት የምናሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ የምናሴም ወንድም የኤፍሬም ልጆች ሱታላና ጠኀን ናቸው። የሱታላ ልጅም ኤዴን ነው።
ከዚህም ነገር በኋላ እንዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባታችን ደከመ” ብለው ለዮሴፍ ነገሩት፤ እርሱም ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።
አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።
ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ፋሲካ ያደርጉ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግሞም ወደ ኤፍሬምና ወደ ምናሴ ደብዳቤዎችን ጻፈ።
የአሴር ልጆች በየወገናቸው፤ ከኢያምን የኢያምናውያን ወገን፥ ከኢያሱ የኢያሱያውያን ወገን፥ ከበርያ የበርያውያን ወገን።