የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ ዘመ​ንህ አለፈ፤ ያል​ተ​ወ​ረ​ሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀር​ታ​ለች፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢያሱ በሸመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፣ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፤ “እነሆ አርጅተሃል፤ ዕድሜህም ገፍቷል፤ ነገር ግን መያዝ ያለበት እጅግ በጣም ሰፊ ምድር ገና አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም ሸመገለ ዕድሜውም ስለ ገፋ አረጀ፤ ጌታም እንዲህ አለው፦ “አንተ ሸምግለሃል፥ ዕድሜህም ስለ ገፋ አርጅተሃል፤ ያልተወረሰ እጅግ ብዙ ምድር ገና ይቀራል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነሆ፥ ኢያሱ በዕድሜ እየገፋ ስለ ሄደ አረጀ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፤ ዕድሜህም ገፍቶአል፤ ገና ብዙ ያልተያዙ ቦታዎች አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም ሸመገለ በዕድሜም አረጀ፥ እግዚአብሔርም አለው፦ አንተ ሸመገልህ፥ በዕድሜህም አረጀህ፥ ያልተወረሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርታለች፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 13:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሣራም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆማ ሳለች ይህን ሰማች። አብ​ር​ሃ​ምና ሣራም በዕ​ድ​ሜ​ያ​ቸው ሸም​ግ​ለው ፈጽ​መው አር​ጅ​ተው ነበር፤ በሴ​ቶች የሚ​ሆ​ነ​ውም ልማድ ከሣራ ተቋ​ርጦ ነበር።


ንጉሡ ዳዊ​ትም አረጀ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ ልብ​ስም ይደ​ር​ቡ​ለት ነበር፤ ነገር ግን አይ​ሞ​ቀ​ውም ነበር።


ዳር​ቻ​ውም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ይወ​ር​ዳል፤ መው​ጫ​ውም በጨው ባሕር ይሆ​ናል። ምድ​ራ​ችሁ እንደ ዳር​ቻዋ በዙ​ሪ​ያዋ ይህች ናት።”


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ እነሆ እና​ንተ ወደ ከነ​ዓን ምድር ትገ​ባ​ላ​ችሁ፤ የከ​ነ​ዓ​ንም ምድር ከአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ችዋ ጋር ለእ​ና​ንተ ርስት ትሆ​ና​ለች።


ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ በፊ​ትህ ያል​ፋል፤ እርሱ እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ትወ​ር​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ኢያሱ በፊ​ትህ ይሄ​ዳል።


የቀ​ረ​ች​ውም ምድር ይህች ናት፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ የጌ​ሴ​ር​ያ​ው​ያ​ንና የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሀገር ሁሉ፥


አሁ​ንም፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ፥ እስ​ራ​ኤል በም​ድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተና​ገ​ረኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አርባ አም​ስት ዓመ​ታት በሕ​ይ​ወት አኖ​ረኝ፤ አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማ​ንያ አም​ስት ዓመት ሆነኝ።


ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አላ​ቸው፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር እን​ዳ​ት​ወ​ር​ሱ​አት እስከ መቼ ድረስ ታቈ​ዩ​አ​ታ​ላ​ችሁ?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድ​ሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆ​ነው ሞተ።