Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም፥ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ፥ እስ​ራ​ኤል በም​ድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተና​ገ​ረኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አርባ አም​ስት ዓመ​ታት በሕ​ይ​ወት አኖ​ረኝ፤ አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማ​ንያ አም​ስት ዓመት ሆነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “አሁንም እነሆ፤ ልክ እግዚአብሔር እንዳለው ይህን ለሙሴ ከተናገረበት ጊዜ አንሥቶ እስራኤል በምድረ በዳ ሲንከራተት እኔን አርባ ዐምስት ዓመት በሕይወት ጠብቆ አኑሮኛል፤ ይኸው ዛሬ ሰማንያ ዐምስት ዓመት ሆነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ ጌታ ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረው ጌታ እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ፤ እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ እኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እስራኤል በምድረ በዳ በጉዞ ላይ ሆኖ ሳለ እግዚአብሔር ሙሴን ይህን ቃል ከተናገረበት ቀን ጀምሮ አሁን እንደምታየኝ እግዚአብሔር እንዳለው ይህን አርባ አምስት ዓመት ጠብቆ አኑሮኛል፤ እነሆ አሁን እኔ ሰማኒያ አምስት ዓመት ሆነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ፥ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 14:10
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ላይ ታላቅ ናትና፥ እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ድረስ ነውና።


ኃጥ​ኣን እንደ ሣር በበ​ቀሉ ጊዜ፥ ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉም ሁሉ በለ​መ​ለሙ ጊዜ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም እን​ደ​ሚ​ጠፉ ነው።


ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር በእ​ር​ስዋ አስ​ቀ​ም​ጣ​ችሁ ዘንድ እጄን ዘር​ግቼ ወደ ማል​ሁ​ላ​ችሁ ምድር በእ​ው​ነት እና​ንተ አት​ገ​ቡም።


ነገር ግን ምድ​ሪ​ቱን ሊሰ​ልሉ ከሄዱ ሰዎች የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ በሕ​ይ​ወት ኖሩ።


ኢያ​ሱም ብዙ ዘመን ከእ​ነ​ዚሁ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር።


ኢያ​ሱም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን አለው፥ “እነሆ ዘመ​ንህ አለፈ፤ ያል​ተ​ወ​ረ​ሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀር​ታ​ለች፤


ሙሴም በላ​ከኝ ጊዜ ጽኑዕ እንደ ነበ​ርሁ፥ ዛሬም ገና እን​ዲሁ ለመ​ዋ​ጋት ለመ​ው​ጣ​ትም ለመ​ግ​ባ​ትም ጽኑዕ ነኝ።


ሙሴም በዚያ ቀን፦ ‘አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽ​መህ ተከ​ት​ለ​ሃ​ልና እግ​ርህ የረ​ገ​ጠው ምድር ለአ​ን​ተና ለል​ጆ​ችህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በር​ግጥ ርስት ይሆ​ናል’ ብሎ ማለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች