የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮናስ 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “በውኑ ስለ​ዚች ቅል ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ሞት ድረስ እጅግ አዝ​ኛ​ለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ግን ዮናስን፣ “በውኑ ስለ ቅሉ ልትቈጣ ይገባሃልን?” አለው። እርሱም፣ “በርግጥ እስከ ሞት ልቈጣ ይገባኛል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔርም ዮናስን “ስለዚች የጉሎ ተክል ልትቆጣ ይገባህልን?” አለው። እርሱም፦ “እስከ ሞት ድረስ ልቆጣ ይገባኛል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም “ስለዚህች ቅል ልትበሳጭ ይገባሃልን?” አለው። ዮናስም “በእርግጥ መበሳጨት ይገባኛል፤ እንዲያውም በንዴት እስከምሞት ድረስ መበሳጨት አለብኝ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮናስ 4:9
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡ አክ​ዓ​ብም መልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ! አንተ እን​ዳ​ልህ፤ እኔ የአ​ንተ ነኝ፤ ለእ​ኔም የሆ​ነው ሁሉ የአ​ንተ ነው” አለ።


መከ​ራው ይገ​ባ​ሃል፤ አን​ተስ የሞ​ትህ እንደ ሆነ ምን​ድን ነው? ከሰ​ማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችን? ወይስ ተራ​ራ​ዎች ከመ​ሠ​ረ​ታ​ቸው ይና​ወ​ጣ​ሉን?


ይበ​ድሉ ዘንድ በተ​ቀ​በ​ሉት መማ​ለጃ ኀጢ​አት ምክ​ን​ያት ቍጣ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ትመ​ጣ​ለች።


ሰነ​ፉን ሰው ቍጣ ይገ​ድ​ለ​ዋ​ልና፥ ቅን​ዓ​ትም ሰነ​ፉን ያጠ​ፋ​ዋል።


ዮና​ስም ፈጽሞ አዘነ፤ ተከ​ዘም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አንተ ትበ​ቅል ዘንድ ላል​ደ​ከ​ም​ህ​ባት፥ ላላ​ሳ​ደ​ግ​ሃ​ትም፥ በአ​ንድ ሌሊት ለበ​ቀ​ለች፥ በአ​ንድ ሌሊ​ትም ለደ​ረ​ቀ​ችው ቅል አዝ​ነ​ሃል።


ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።


“ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ፤ ከእኔም ጋር ትጉ፤” አላቸው።


ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተብሎ የሚ​ደ​ረግ ኀዘን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የሚ​ያ​ሰጥ ንስሓ ነው። ስለ ዓለም የሚ​ደ​ረግ ኀዘን ግን ሞትን ያመ​ጣል።


በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ አያገኙትምም፤ ሊሞቱም ይመኛሉ፤ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።


ከዚ​ህም በኋላ ሌሊ​ቱን ሁሉ በነ​ገር በዘ​በ​ዘ​በ​ች​ውና በአ​ደ​ከ​መ​ችው ጊዜ፥ ልሙት እስ​ኪል ድረስ ተበ​ሳጨ።