Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮናስ 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እግዚአብሔርም ዮናስን “ስለዚች የጉሎ ተክል ልትቆጣ ይገባህልን?” አለው። እርሱም፦ “እስከ ሞት ድረስ ልቆጣ ይገባኛል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔር ግን ዮናስን፣ “በውኑ ስለ ቅሉ ልትቈጣ ይገባሃልን?” አለው። እርሱም፣ “በርግጥ እስከ ሞት ልቈጣ ይገባኛል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔርም “ስለዚህች ቅል ልትበሳጭ ይገባሃልን?” አለው። ዮናስም “በእርግጥ መበሳጨት ይገባኛል፤ እንዲያውም በንዴት እስከምሞት ድረስ መበሳጨት አለብኝ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “በውኑ ስለ​ዚች ቅል ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ሞት ድረስ እጅግ አዝ​ኛ​ለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮናስ 4:9
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቁጣ ወርሶሃል፥ ስለ አንተ ሲባል፥ ምድር ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለት ከስፋራው ይነቀላልን?”


አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።


በሕይወት መኖሩን እስኪጠላ ድረስ ዕለት ዕለት በመጨቅጨቅ አሰለቸችው።


በዚያም ቀኖች ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ አያገኙትምም፤ ሊሞቱም ይመኛሉ፤ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።


እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ወደ መዳን ለሚያደርስ ንስሓ ያበቃል፤ ጸጸትም የለበትም፤ ዓለማዊው ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።


“ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝናለች፤ እዚህ ቆዩ፤ ከእኔም ጋር ትጉ” አላቸው።


ሀብት ወደ ስድብ አስቶ እንዳይወስድህ፥ ትልቅ ጉቦም ከመስመር እንዳያስወጣህ።


ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፥ ክፉኛም አበሳጨው።


ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።


ጌታም እንዲህ አለው፦ “አንተ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው የጉሎ ተክል አዝነሃል።


የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ እንዳልህ ነው፥ እኔ ለእኔም የሆነው ሁሉ የአንተ ነው” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች