የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በኢየሩሳሌም፣ በበጎች በር አጠገብ፣ ዐምስት ባለመጠለያ መመላለሻዎች የነበሯት፣ በአራማይክ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የተባለች አንዲት መጠመቂያ አለች።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ፥ በዕብራይስጥ ቋንቋ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ የምንጭ ኲሬ ነበረ፤ በዙሪያውም አምስት ከላይ ክዳን ያላቸው መተላለፊያዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 5:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከኤ​ፍ​ሬ​ምም በር በላይ፥ በአ​ሮ​ጌው በርና በዓሣ በር፥ በአ​ና​ን​ኤ​ልም ግንብ፥ በሃ​ሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘ​በ​ኞ​ችም በር አጠ​ገብ ቆሙ።


ታላ​ቁም ካህን ኤል​ያ​ሴ​ብና ወን​ድ​ሞቹ ካህ​ናት ተነ​ሥ​ተው የበግ በር ሠሩ፤ ቀደ​ሱ​ትም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆሙ፤ እስከ መቶ ግን​ብና እስከ ሐና​ን​ኤል ግንብ ድረስ ቀደ​ሱት።


ከማ​ዕ​ዘ​ኑም መውጫ ጀም​ረው እስከ በጎች በር ድረስ ወርቅ አን​ጥ​ረ​ኞ​ችና ነጋ​ዴ​ዎች ሠሩ።


በአ​ሮ​ጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁ​ለቱ ቅጥር መካ​ከል መከ​ማቻ ሠራ​ችሁ፤ ይህን ያደ​ረ​ገ​ውን ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ች​ሁም፤ ቀድሞ የሠ​ራ​ው​ንም አላ​ያ​ች​ሁም።


የዳ​ዊ​ትም ከተማ ፍራ​ሾች እን​ደ​በዙ አይ​ታ​ች​ኋል፤ የታ​ች​ኛ​ው​ንም ኵሬ ውኃ በከ​ተማ አከ​ማ​ች​ታ​ች​ኋል፤


ጲላ​ጦ​ስም ይህን ሰምቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ውጭ አወ​ጣው፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ገበታ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው “ጸፍ​ጸፍ” በሚ​ሉት ቦታ ላይ በወ​ን​በር ተቀ​መጠ።


መስ​ቀ​ሉ​ንም ተሸ​ክሞ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ጎል​ጎታ ወደ ተባ​ለው ቀራ​ንዮ ወደ​ሚ​ባል ቦታ ወጣ።


ከአ​ይ​ሁ​ድም ይህ​ቺን ጽሕ​ፈት ያነ​በ​ብ​ዋት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን የሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ለከ​ተማ ቅርብ ነበ​ርና፤ ጽሕ​ፈ​ቱም የተ​ጻ​ፈው በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ፥ በሮ​ማ​ይ​ስ​ጥና በግ​ሪክ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማር​ያም!” አላት፤ እር​ስ​ዋም መለስ ብላ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ፥ “ረቡኒ!” አለ​ችው፤ ትር​ጓ​ሜ​ዉም “መም​ህር” ማለት ነው።


በዚ​ያም ዕው​ሮ​ችና አን​ካ​ሶች፥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም የሰ​ለለ ብዙ ድው​ያን ተኝ​ተው የው​ኃ​ዉን መና​ወጥ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አላ​ቸው፥ “አንድ ሥራ ሠራሁ፤ ሁላ​ች​ሁም አደ​ነ​ቃ​ችሁ።


በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።


በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።


በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው፤ እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል።